አዝ፦ አምላኬ ፡ ያደረገውን ፡ ሁሉ ፡ ባወራው
ባወራው ፡ ባወራው ፡ ባወራው
ከቁጥር ፡ ሁሉ ፡ በዛ ፡ ተዓምራቱ
ብዙ ፡ ነው ፡ ባወራው (፪x)
ኃጢአተኛ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ አይቼ
እንደ ፡ ሊባኖስ ፡ ዛፍ ፡ ለምልሞ ፡ ፈርቼ
ተመልሼ ፡ ከቦታው ፡ ፈለግሁት
እንኳን ፡ እርሱን ፡ ስፍራውን ፡ አጣሁት
አዝ፦ አምላኬ ፡ ያደረገውን ፡ ሁሉ ፡ ባወራው
ባወራው ፡ ባወራው ፡ ባወራው
ከቁጥር ፡ ሁሉ ፡ በዛ ፡ ተዓምራቱ
ብዙ ፡ ነው ፡ ባወራው (፪x)
የክፉ ፡ ኃይል ፡ በቁጣ ፡ ዓይኖቼ ፡ እያየኝ
ጥርሱን ፡ በላዬ ፡ ላይ ፡ ስያንገጫግጭብኝ
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ አይቶ ፡ ስቆበታል
የመትፍያው ፡ ቀን ፡ እንደደረሰ ፡ አውቋል
አዝ፦ አምላኬ ፡ ያደረገውን ፡ ሁሉ ፡ ባወራው
ባወራው ፡ ባወራው ፡ ባወራው
ከቁጥር ፡ ሁሉ ፡ በዛ ፡ ተዓምራቱ
ብዙ ፡ ነው ፡ ባወራው (፪x)
ከመቅደሱ ፡ ከሰማይ ፡ ከፍታ ፡ ላይ ፡ ሆኗል
ወደ ፡ ምድር ፡ በታች ፡ አሽቆልቁሎ ፡ አይቷል
የእስረኞቹን ፡ የጩኸት ፡ ቃል ፡ ሰምቷል
ከሞት ፡ አፋፍ ፡ ከፍርድ ፡ ወጥመድ ፡ ፈቷል
አዝ፦ አምላኬ ፡ ያደረገውን ፡ ሁሉ ፡ ባወራው
ባወራው ፡ ባወራው ፡ ባወራው
ከቁጥር ፡ ሁሉ ፡ በዛ ፡ ተዓምራቱ
ብዙ ፡ ነው ፡ ባወራው (፪x)
ከሰይጣን ፡ ኃይል ፡ የዳንህ ፡ ወገን ፡ ሁሉ ፡ ከሰይፍ
ለሚመጣው ፡ ትውልድ ፡ ጻፍና ፡ አስተላልፍ
አምላካችን ፡ ይህን ፡ ተአምር ፡ ሰርቷል
እኔም ፡ ባወራ ፡ ባወራው ፡ በዝቷል
አዝ፦ አምላኬ ፡ ያደረገውን ፡ ሁሉ ፡ ባወራው
ባወራው ፡ ባወራው ፡ ባወራው
ከቁጥር ፡ ሁሉ ፡ በዛ ፡ ተዓምራቱ
ብዙ ፡ ነው ፡ ባወራው (፪x)