Yebazenewin Felagi Amlak (የባዘነውን ፡ ፈላጊ ፡ አምላክ)

<poem>
የጠራውን ፡ መስሎ ፡ መኖር ፡ መጋደሉን ፡ ፈርቶ
የገባለትን ፡ ቃልና ፡ ተስፋውን ፡ ዘንግቶ
የሙት ፡ ልጅ ፡ የነበረ ፡ ሰው ፡ ከጥፋት ፡ የዳነ
የተሰዋለትን ፡ ኢየሱስ ፡ ያንን ፡ አዳኙን ፡ ከዳ

:<u>አዝ</u>፦ የባዘነውን ፡ ፋላጊ ፡ አምላክ
::የምህረት ፡ አምባ ፡ ለጠፉትም ፡ የምታነባ
::ከሕይወት ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ከእረፍት ፡ ወደ ፡ ጭንቀት
::የሄደውን ፡ መልስ ፡ እባክህ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ መንጋህ ፡ በረት

ተዋግቶ ፡ የማረከውን ፡ ያንን ፡ ስመ ፡ ጥሩ ፡ ጀግና
ጌታውን ፡ ሊያስከብር ፡ ቆርጦ ፡ ተሰልፏልና
ጠላት ፡ ከባሻገር ፡ ቆሞ ፡ ቅናት ፡ እያጋየው
እሸክላውን ፡ ዘርግቶበት ፡ ወንድሜን ፡ ዘለፈው

:<u>አዝ</u>፦ የባዘነውን ፡ ፋላጊ ፡ አምላክ
::የምህረት ፡ አምባ ፡ ለጠፉትም ፡ የምታነባ
::ከሕይወት ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ከእረፍት ፡ ወደ ፡ ጭንቀት
::የሄደውን ፡ መልስ ፡ እባክህ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ መንጋህ ፡ በረት

በአምላኩ ፡ መቅደስ ፡ ውስጥ ፡ ሆኖ ፡ ተማምኖ ፡ እያገሳ
ገናናነቱንም ፡ ሲያውጅ ፡ የይሁዳን ፡ አንበሳ
እንግዳ ፡ ነገር ፡ ወሰደው ፡ ነዝንዞ ፡ ጨቅጭቆ
ፀጋ ፡ ክብሩን ፡ አስላጭቶ ፡ እጅግ ፡ አስጨንቆ

:<u>አዝ</u>፦ የባዘነውን ፡ ፋላጊ ፡ አምላክ
::የምህረት ፡ አምባ ፡ ለጠፉትም ፡ የምታነባ
::ከሕይወት ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ከእረፍት ፡ ወደ ፡ ጭንቀት
::የሄደውን ፡ መልስ ፡ እባክህ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ መንጋህ ፡ በረት

ጥቃቅኑ ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ጉልበቱን ፡ ከርክሮ
ጤናውን ፡ እየሰቀረበት ፡ በህመም ፡ አደንዝዞ
ያ ፡ የክህደት ፡ አውሎ ፡ በሕይወቱ ፡ ነፍሶበት
ከወይኑ ፡ ግንድ ፡ ገነጠለው ፡ ፍሬ ፡ እንዳይገኝበት

:<u>አዝ</u>፦ የባዘነውን ፡ ፈላጊ ፡ አምላክ
::የምህረት ፡ አምባ ፡ ለጠፉትም ፡ የምታነባ
::ከሕይወት ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ከእረፍት ፡ ወደ ፡ ጭንቀት
::የሄደውን ፡ መልስ ፡ እባክህ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ መንጋህ ፡ በረት
</poem>

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue