Ya hulu alefena (ያ ፡ ሁሉ ፡ አለፈና)

አዝ፦ እንደማያልፍ ፡ የለም ፡ ያሁሉ ፡ አለፈና
የሰቆቃው ፡ ዘመን ፡ በደስታ ፡ ተተካ ፡ አሜን
አንገቴን ፡ ደፍቼ ፡ የሰው ፡ ፊት ፡ ፈርቼ
ያለፍኩበት ፡ ዘመን ፡ ዘለፋ ፡ ጠግቤ ፡ አቤት
በቃ ፡ ሲለኝ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ ገደል ፡ ገባ
የጐበጠ ፡ አንገቴ ፡ ለምሥጋና ፡ ቀና ፡ አሜን (፪x)

ምሥጋናዬ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ምሥጋናዬ
አሰዋለሁ ፡ ዛሬ ፡ በኮረብታ ፡ ቆሜ
ነጻ ፡ ወጥቼ ፡ ነጻ ፡ ሰው ፡ መሆን ፡ ችያለሁ
በክርስቶስ ፡ ዛሬ ፡ ትልቅ ፡ ተብያለሁ
የናቁኝም ፡ ያኔ ፡ አንቅረው ፡ የተፉኝ
ጐንበስ ፡ አሉ ፡ ጐንበስ ፡ ጌታ ፡ አክብሮኝ ፡ ሲያዩኝ

አዝ፦ እንደማያልፍ ፡ የለም ፡ ያሁሉ ፡ አለፈና
የሰቆቃው ፡ ዘመን ፡ በደስታ ፡ ተተካ ፡ አሜን
አንገቴን ፡ ደፍቼ ፡ የሰው ፡ ፊት ፡ ፈርቼ
ያለፍኩበት ፡ ዘመን ፡ ዘለፋ ፡ ጠግቤ ፡ አቤት
በቃ ፡ ሲለኝ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ ገደል ፡ ገባ
የጐበጠ ፡ አንገቴ ፡ ለምሥጋና ፡ ቀና ፡ አሜን

አሁን ፡ ይኸው ፡ እንዲህ ፡ እንዲህ ፡ አምሮብኛል
አፌም ፡ በዝማሬ ፡ በዘይት ፡ ታብሷል
ማንም ፡ አልጠበቀኝ ፡ እኔን ፡ ለቁም ፡ ነገር
ጌታ ፡ ሲያረገው ፡ ግን ፡ ማነው ፡ የሚናገር
ምስኪኖች ፡ ሆይ ፡ በርቱ ፡ ጌታ ፡ አይጥላችሁም/ሰውን ፡ አይጥልም
ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ በዓይኔ ፡ ስላየሁኝ (፪x)

አዝ፦ እንደማያልፍ ፡ የለም ፡ ያሁሉ ፡ አለፈና
የሰቆቃው ፡ ዘመን ፡ በደስታ ፡ ተተካ ፡ አሜን
አንገቴን ፡ ደፍቼ ፡ የሰው ፡ ፊት ፡ ፈርቼ
ያለፍኩበት ፡ ዘመን ፡ ዘለፋ ፡ ጠግቤ ፡ አቤት
በቃ ፡ ሲለኝ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ ገደል ፡ ገባ
የጐበጠ ፡ አንገቴ ፡ ለምሥጋና ፡ ቀና ፡ አሜን

ያኔ ፡ ያሰብኩት ፡ ሁሉ ፡ ወደ ፡ ገደል ፡ ገብቷል
አሁን ፡ በሕይወቴ ፡ ዛሬ ፡ አካሌ ፡ ቆሟል
ወገኖችም ፡ በቃ ፡ ብለው ፡ ነበር ፡ በቃ
በሃያሉ ፡ ኢየሱስ ፡ ከመቃብር ፡ ወጣሁ
እግሬም ፡ እንደዋላ ፡ አግሮች ፡ በርትተዋል
አፌም ፡ በዝማሬ ፡ በዘይት ፡ ታብሷል

አዝ፦ እንደማያልፍ ፡ የለም ፡ ያሁሉ ፡ አለፈና
የሰቆቃው ፡ ዘመን ፡ በደስታ ፡ ተተካ ፡ አሜን
አንገቴን ፡ ደፍቼ ፡ የሰው ፡ ፊት ፡ ፈርቼ
ያለፍኩበት ፡ ዘመን ፡ ዘለፋ ፡ ጠግቤ ፡ አቤት
በቃ ፡ ሲለኝ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ ገደል ፡ ገባ
የጐበጠ ፡ አንገቴ ፡ ለምሥጋና ፡ ቀና ፡ አሜን (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue