Mesgana Ahahatitle (ምሥጋና ፡ አሃሃ)

ገናና ፡ የእኛ ፡ ኢየሱሱ ፡ አቻ ፡ አይገኝለት
እንደሞተ ፡ አልቀረም ፡ ከቶ ፡ አለ ፡ በሰማያት
ማን ፡ ይቃወመናል ፡ ዛሬስ ፡ በደሙ ፡ ዋጅቶናል
ትንሴኤውን ፡ ልናወራ ፡ (በገና ፡ አንስተናል) (፪x)

(ምሥጋና) (፫x) ፡ ለሆነው ፡ ገናና
(ዕልልታ) (፫x) ፡ ድል ፡ ላረገው ፡ ጌታ

ከሰማይ ፡ ሰማያት ፡ ከዙፋኑ ፡ ወርዶ
የዕዳውን ፡ ጽህፈት ፡ በደሙ ፡ አስወግዶ
ምስኪን ፡ መስሎ ፡ መቶ ፡ ዲያብሎስን ፡ ቀጣ
በጨለማ ፡ ላሉ ፡ አዲስ ፡ ፀሐይ ፡ ወጣ

አዝ
ገናና ፡ የእኛ ፡ እየሱስ

ጐስቋላና ፡ ድሃ ፡ ምስኪን ፡ የህማም ፡ ሰው
ባየነውም ፡ ጊዜ ፡ ደም ፡ ግባት ፡ የሌለው
ፍቅር ፡ ኃይሉ ፡ ሆነች ፡ ድካሙ ፡ በረታ
ማንም ፡ ሳያግዘው ፡ ዲያብሎስን ፡ መታ

አዝ
ገናና ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ

የጣር ፡ የሰቆቃው ፡ ጩኸቱ ፡ ሲሰማ
መከራው ፡ በዝቶበት ፡ ቢመስልም ፡ ደካማ
ምድር ፡ አልቻለችም ፡ ሞትን ፡ ፈነቀለ
ተስፋ ፡ ለቆረጡ ፡ አዲስ ፡ ዘር ፡ በቀለ

አዝ
ገናና ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ

ስሙም ፡ ድንቅ ፡ መካር ፡ የሰላም ፡ አለቃ
ሞትና ፡ ርግማንም ፡ ስቃዩ ፡ አበቃ
ገናና ፡ ገናና ፡ገናና ፡ ነው ፡ አሱ
በሆታ ፡ በልልታ ፡ ስሙን ፡ አሞግሱ

አዝ
ገናና ፡ የስኛ ፡ ኢየሱስ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue