ቃልኪዳን ፡ በማፍረስ ፡ አንቺ ፡ የታውክሽው
መሃላን ፡ በመጣል ፡ ቢሆን ፡ የታወክሽው
እኔ ፡ ግን ፡ ኪዳኔን ፡ ዛሬም ፡ አስባለሁ
እኔ ፡ ግን ፡ ኪዳኔን ፡ አጸናልሻለሁ
እያለ ፡ የሚመጣ ፡ ምን ፡ ዓይነት ፡ አምላክ ፡ ነው
እያለ ፡ የሚጠጋ ፡ እውነትም ፡ አምላክ ፡ ነው
ሲያውቀው ፡ የሚጠጋ ፡ ምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው
ወዶ ፡ የማይለወጥ ፡ እውነትም ፡ ወዳጅ ፡ ነው
ጌታዬ ፡ ነው ፡ የሚማልከው
ወዳጄ ፡ ነው ፡ እወደዋለሁ (፪x)