አዝ፦ በቸርነትህ ፡ ዓመታትን ፡ ታቀናጃለህ
በቸርነትህ ፡ ዘመናትን ፡ ታቀናጃለህ
ጌታ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ (፪x)
ምድራችንን ፡ ጐበኘሃት ፡ ምህረትን ፡ ለእርሷ ፡ አደረግህ
ብልጽግናዋን ፡ አበዛህ ፡ ምግቧን ፡ አዘጋጅተህ ፡ ሰጥተህ
. (1) . ፡ በማስተካከል ፡ እውነት ፡ እያለስለስካት
ቡቃያውን ፡ በመባረክ ፡ መልካም ፡ ፍሬን ፡ አጠገብካት (፪x)
አዝ፦ በቸርነትህ ፡ ዓመታትን ፡ ታቀናጃለህ
በቸርነትህ ፡ ዘመናትን ፡ ታቀናጃለህ
ጌታ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ (፪x)
ከክብርህ ፡ ባለጠግነት ፡ ነፍሳችንን ፡ እያጠገብክ
እስከ ፡ ሺ ፡ ትውልድ ፡ በሆነው ፡ በረከትህ ፡ እየባረክ
ሁሉን ፡ ለእኛ ፡ ሰጥተኸናል ፡ የረገጥነውን ፡ ወርሰናል
በስምህ ፡ ስልጣን ፡ በኃይልህ ፡ ሮሆቦት ፡ አሜን ፡ ሰርተናል (፪x)
አዝ፦ በቸርነትህ ፡ ዓመታትን ፡ ታቀናጃለህ
በቸርነትህ ፡ ዘመናትን ፡ ታቀናጃለህ
ጌታ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ (፪x)
የምድርን ፡ አፈር ፡ ባርከኸው ፡ ሰብልን ፡ ይሰጣል ፡ ዛሬ
ጠግበን ፡ ረክተን ፡ እንኖራለን ፡ ለቅሷችን ፡ ሆኗል ፡ ዝማሬ
ወራት ፡ አመት ፡ ዘመናትን ፡ ለልጆችህ ፡ ተሰጥተዋል
ኤልሻዳይ ፡ ንጉሥ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሁሉን ፡ አቀዳጅተኸናል (፪x)
አዝ፦ በቸርነትህ ፡ ዓመታትን ፡ ታቀናጃለህ
በቸርነትህ ፡ ዘመናትን ፡ ታቀናጃለህ
ጌታ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ (፪x)
የምድረበዳ ፡ ተራሮች ፡ በመንፈስ ፡ እውነት ፡ ረክተዋል
ኮረብቶችም ፡ በደስታ ፡ በስምህ ፡ ሀይልን ፡ ታጭቀዋል
የማሰማሪያ ፡ ቦታዋች ፡ በመንጐቹ ፡ ውበት ፡ ለበሱ
ሸለቆ ፡ እህል ፡ ተሞልቶ ፡ ክበር/ድመቅ ፡ ይልሃል ፡ ንጉሡ (፪x)
አዝ፦ በቸርነትህ ፡ ዓመታትን ፡ ታቀናጃለህ
በቸርነትህ ፡ ዘመናትን ፡ ታቀናጃለህ
ጌታ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ (፪x)