Yehiwot Enjera (የሕይወት ፡ እንጀራ)

አዝ፦ በእኛ ፡ ዘንድ ፡ ያለው ፡ የምስራች
የምንተርከው ፡ ለሰው ፡ ልጆች
ለተጠማችሁ ፡ ለተራባችሁ
የሕይወትን ፡ ውኃ ፡ ኑ ፡ እናሳያችሁ
የሕይውትን ፡ እንጀራን ፡ እናካፍላችሁ
የናዝሬቱን ፡ ኢየሱስን
እናውጋላችሁ ፡ ማርካት ፡ ማጥገቡን

እኛስ ፡ ጠጣነው ፡ በላነውና
ከርሃብ ፡ ጥማት ፡ አርፈናልና
ኦ ፡ ያለው ፡ ማርካት ፡ ቃላት ፡ አይገልፀው
ቀምሳችሁ ፡ እዩት ፡ ጌታ ፡ ድንቅ ፡ ነው

አዝ፦ በእኛ ፡ ዘንድ ፡ ያለው ፡ የምስራች
የምንተርከው ፡ ለሰው ፡ ልጆች
ለተጠማችሁ ፡ ለተራባችሁ
የሕይወትን ፡ ውኃ ፡ ኑ ፡ እናሳያችሁ
የሕይውትን ፡ እንጀራን ፡ እናካፍላችሁ
የናዝሬቱን ፡ ኢየሱስን
እናውጋላችሁ ፡ ማርካት ፡ ማጥገቡን

አንዴ ፡ የጠጣ ፡ ከዚህ ፡ ከውኃ
ጥማት ፡ ላይነካው ፡ ቢኖር ፡ በረሃ
ለዘለዓለም ፡ የሚፈልቅ ፡ ከሆዱ
የተጣማችሁ ፡ በነጻ ፡ ቅዱ

አዝ፦ በእኛ ፡ ዘንድ ፡ ያለው ፡ የምስራች
የምንተርከው ፡ ለሰው ፡ ልጆች
ለተጠማችሁ ፡ ለተራባችሁ
የሕይወትን ፡ ውኃ ፡ ኑ ፡ እናሳያችሁ
የሕይውትን ፡ እንጀራን ፡ እናካፍላችሁ
የናዝሬቱን ፡ ኢየሱስን
እናውጋላችሁ ፡ ማርካት ፡ ማጥገቡን

ከዚህ ፡ ከውኃ ፡ ከማርካት ፡ ኃይሉ
ፍሬያቸው ፡ በዛ ፡ የጠጡ ፡ ሁሉ
ሥርን ፡ ሰደዱ ፡ አይናወጡ
በጋው ፡ ሲመጣ ፡ አልደነገጡ

አዝ፦ በእኛ ፡ ዘንድ ፡ ያለው ፡ የምስራች
የምንተርከው ፡ ለሰው ፡ ልጆች
ለተጠማችሁ ፡ ለተራባችሁ
የሕይወትን ፡ ውኃ ፡ ኑ ፡ እናሳያችሁ
የሕይውትን ፡ እንጀራን ፡ እናካፍላችሁ
የናዝሬቱን ፡ ኢየሱስን
እናውጋላችሁ ፡ ማርካት ፡ ማጥገቡን

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue