Ante bicha sew taderegaleh (አንተ ፡ ብቻ ፡ ሰው ፡ ታደርጋለህ)

አዝ፦ አንተ ፡ ብቻ ፡ ሰው ፡ ታደርጋለህ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ትለዉጣለህ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ትሸከማለህ
አንተ ፡ ብቻ ፡ አሃ ፡ ታሳርፋለህ ፡ ታሳርፋለህ
ለዘለዓለም ፡ ተመስገን
ክበር ፡ ክበር ፡ ኢየሱስ ፡ ክበር
ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ

ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
የልብን ፡ ስብራት ፡ ቁስል ፡ ሚፈውስ
ስብራት ፡ ሚጠግን ፡ መልካም ፡ መዓዛ ፡ አለው
ስምህ ፡ ብቻውን ፡ ፍፁም ፡ መዳህኒት ፡ ነው
ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ እያሱስ ፡ ተባረክ (፪x)

በእርባን ፡ እንዲፈታ ፡ ኢየሱስ ፡ ታሰርህ
አቅም ፡ እያለህ ፡ ደካማ ፡ መሰልህ
ጻዲቁ ፡ ኢየሱስ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ውለህ
በፍቅርህ ፡ ብቻ ፡ ስንቱን ፡ እረታህ
ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ (፪x)

አዝ፦ አንተ ፡ ብቻ ፡ ሰው ፡ ታደርጋለህ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ትለዉጣለህ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ትሸከማለህ
አንተ ፡ ብቻ ፡ አሃ ፡ ታሳርፋለህ ፡ ታሳርፋለህ
ለዘለዓለም ፡ ተመስገን
ክበር ፡ ክበር ፡ ኢየሱስ ፡ ክበር
ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ

አየሁኝ ፡ እኔም ፡ አየሁኝ
አየሁኝ ፡ እኔም ፡ አየሁኝ ፡ ለክብርህ ፡ ተንበረከኩኝ
ቀመስኩኝ ፡ እኔም ፡ ቀመስኩኝ
ቀመስኩኝ ፡ እኔም ፡ ቀመስኩኝ ፡ ለፍቅርህ ፡ ተንበረከኩኝ
ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ

ቀራጭ ፡ አመንዝራ ፡ ብለህ ፡ ሳትለይ
ከእስራት ፡ ልትፈታ ፡ የምትጐበኝ
በደምህ ፡ እያነጻህ ፡ ታሪክ ፡ የምትለውጥ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ሰላምን ፡ የምትሰጥ
ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ (፪x)

አየሁኝ ፡ እኔም ፡ አየሁኝ
አየሁኝ ፡ እኔም ፡ አየሁኝ ፡ ለክብርህ ፡ ተንበረከኩኝ
ቀመስኩኝ ፡ እኔም ፡ ቀመስኩኝ
ቀመስኩኝ ፡ እኔም ፡ ቀመስኩኝ ፡ ለፍቅርህ ፡ ተንበረከኩኝ
ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ

ተስፋ ፡ ለቆረጠው ፡ ተስፋ ፡ ትሆናለህ
የተሰወረውን ፡ ሁሉ ፡ ትገልጻለህ
ኃይልም ፡ ለሌለው ፡ ብርታት ፡ ትሆናለህ
አንተ ፡ ብቻህን ፡ ድንቅን ፡ ታደጋለህ
ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ እያሱስ ፡ ትባረክ (፪x)

አዝ፦ አንተ ፡ ብቻ ፡ ሰው ፡ ታደርጋለህ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ትለዉጣለህ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ትሸከማለህ
አንተ ፡ ብቻ ፡ አሃ ፡ ታሳርፋለህ ፡ ታሳርፋለህ
ለዘለዓለም ፡ ተመስገን
ክበር ፡ ክበር ፡ ኢየሱስ ፡ ክበር
ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue