Kebrehen Lawra (ክብርህን ፡ ላውራ)

የቱን ፡ ጀምሬ ፡ የቱን ፡ ልተወው
ይሄ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው
ያደረገውን ፡ ሳስበው ፡ ሳስበው
ከቁጥር ፡ በላይ ፡ ነው
ለእኔ ፡ የሆነውን ፡ ሳስበው ፡ ሳስበው
ከቁጥር ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)

አቤት ፡ በአንተ ፡ ስንቱን ፡ አለፍኩኝ
የጠላቴን ፡ ጉልበት ፡ ረገጥኩኝ
ጌታ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
የጠላት ፡ ምሽግ ፡ ገና ፡ ይፈርሳል

ክብርህን ፡ ላውራ ፡ ዛሬም ፡ ነገም
የእስራኤል ፡ ቅዱስ ፡ አንተው ፡ ተባረክ
ብዙ ፡ ስራዬን ፡ አንተ ፡ ሰርተሃል
አመልክህ ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል (፪x)

ከአንተ ፡ በአንተ ፡ በሆነው ፡ ነገር
እዚህ ፡ ደረስኩ ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ
ደስታዬ ፡ ይኸው ፡ ፍፁም ፡ ሆነልኝ
አማኑኤል ፡ ክበርልኝ

የቱን ፡ ጀምሬ ፡ የቱን ፡ ልተወው
ይሄ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው
ያደረገውን ፡ ሳስበው ፡ ሳስበው
ከቁጥር ፡ በላይ ፡ ነው
ለእኔ ፡ የሆነውን ፡ ሳስበው ፡ ሳስበው
ከቁጥር ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)

Recently Listened by

1 comments

:: / ::
::
/ ::

Queue