አዝ፦ ልዑል ፡ ተወለደ ፡ በቤተልሔም
የፍጥረታት ፡ ቤዛ ፡ መድኃኒያለም
ክብር ፡ በአርያም ፡ ይሁን ፡ ለእግዚአብሔር
ወድቋል ፡ ከላያችን ፡ የሞት ፡ ፍርሃት ፡ ቀንበር
በግርግም ፡ ተወልዶ ፡ በመስቀል ፡ ሊሰቀል
የዓለምን ፡ ሁሉ ፡ ኃጢአት ፡ እርሱ ፡ ለመቀበል
አማኑኤል ፡ መጥቶአል ፡ ከአምላክ ፡ ሊያስታርቀን
ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን
አዝ፦ ልዑል ፡ ተወለደ ፡ በቤተልሔም
የፍጥረታት ፡ ቤዛ ፡ መድኃኒያለም
ክብር ፡ በአርያም ፡ ይሁን ፡ ለእግዚአብሔር
ወድቋል ፡ ከላያችን ፡ የሞት ፡ ፍርሃት ፡ ቀንበር
ከአርያም ፡ ተላከ ፡ የምስራች ፡ ወንጌል
በበረት ፡ እንዳለ ፡ የልዑላን ፡ ልዑል
በድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ለምንኖር ፡ ሁሉ
ብርሃን ፡ ወጥቶልናል ፡ ሃሌሉያ ፡ በሉ
አዝ፦ ልዑል ፡ ተወለደ ፡ በቤተልሔም
የፍጥረታት ፡ ቤዛ ፡ መድኃኒያለም
ክብር ፡ በአርያም ፡ ይሁን ፡ ለእግዚአብሔር
ወድቋል ፡ ከላያችን ፡ የሞት ፡ ፍርሃት ፡ ቀንበር
የጥልን ፡ ግድግዳ ፡ ለማፍረስ ፡ ወረደ
በበረት ፡ ተወልዶ ፡ እራሱን ፡ አዋረደ
ወደረኞቻችን ፡ አዩ ፡ ደስታችንን
አማኑኤል ፡ ፅድቃችን ፡ ሆኖ ፡ ሲታደገን
አዝ፦ ልዑል ፡ ተወለደ ፡ በቤተልሔም
የፍጥረታት ፡ ቤዛ ፡ መድኃኒያለም
ክብር ፡ በአርያም ፡ ይሁን ፡ ለእግዚአብሔር
ወድቋል ፡ ከላያችን ፡ የሞት ፡ ፍርሃት ፡ ቀንበር
መላዕክት ፡ በሰማይ ፡ ክብርን ፡ ለአምላክ ፡ ሰጡ
ሰብአሰገልም ፡ ከሩቅ ፡ አገር ፡ መጡ
እጣንና ፡ ከርቤን ፡ ወርቅ ፡ አቀረቡለት
በበረት ፡ ለተኛው ፡ ለዓለም ፡ መድኃኒት
አዝ፦ ልዑል ፡ ተወለደ ፡ በቤተልሔም
የፍጥረታት ፡ ቤዛ ፡ መድኃኒያለም
ክብር ፡ በአርያም ፡ ይሁን ፡ ለእግዚአብሔር
ወድቋል ፡ ከላያችን ፡ የሞት ፡ ፍርሃት ፡ ቀንበር