Tsadik bemnet behiwet (ጻድቅ ፡ ግን ፡ በእምነት)

ሄኖክ ፡ ሞትን ፡ እንዳያይ ፡ በእምነት ፡ ተወሰደ
ኖህ ፡ በምድረ ፡ በዳው ፡ መርከብን ፡ አበጀ
አብረሃም ፡ እርስቱን ፡ ከነዓንን ፡ ወረሰ
ሳራም ፡ በእምነቷ ፡ ኃይሏ ፡ ተመለሰ

አዝ፦ ጻድቅ ፡ ግን ፡ በእምነት ፡ በሕይወት ፡ ይኖራል
የሚታየውን ፡ ሳይሆን ፡ የማይታየውን ፡ ይረዳል
የተስፋውን ፡ ቃል ፡ የሰጠው ፡ የታመነ ፡ ነውና
ደካሞች ፡ በእምነት ፡ ጉልበታችሁ ፡ ይጽና (፪x)

ነፍሱ ፡ ፍፁም ፡ ደክማ ፡ ትንፋሽ ፡ ተሰውሮ
የሚታይ ፡ መመኪያ ፡ ከአፈር ፡ ተቀብሮ
ሥጋ ፡ ደግሞ ፡ ዝሎ ፡ ሞት ፡ ሽታ ፡ ሲሸተው
ጻድቅ ፡ ግን ፡ በእምነት ፡ ከክርስቶስ ፡ ጋር ፡ ነው

አዝ፦ ጻድቅ ፡ ግን ፡ በእምነት ፡ በሕይወት ፡ ይኖራል
የሚታየውን ፡ ሳይሆን ፡ የማይታየውን ፡ ይረዳል
የተስፋውን ፡ ቃል ፡ የሰጠው ፡ የታመነ ፡ ነውና
ደካሞች ፡ በእምነት ፡ ጉልበታችሁ ፡ ይጽና (፪x)

ባሕሩን ፡ በበትር ፡ አሻግሮ ፡ የከፈለ
ውሃን ፡ እንደ ፡ ግድግዳ ፡ ገትሮ ፡ ያቆመ
ዝናብን ፡ ኤልያስ ፡ በእምነት ፡ ከለከለ
እስራኤል ፡ በአምላኩ ፡ ጉልበቱ ፡ አየለ

አዝ፦ ጻድቅ ፡ ግን ፡ በእምነት ፡ በሕይወት ፡ ይኖራል
የሚታየውን ፡ ሳይሆን ፡ የማይታየውን ፡ ይረዳል
የተስፋውን ፡ ቃል ፡ የሰጠው ፡ የታመነ ፡ ነውና
ደካሞች ፡ በእምነት ፡ ጉልበታችሁ ፡ ይጽና (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue