Seletederegelgne Begonet (ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት )

አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x)

ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)
አመሰግንሃለው (፮x)

እንደ ፡ ባለማዕረግ ፡ ሰው ፡ ተመልክተኸኝ
የማይገባኝን ፡ ክብርን ፡ ሰጥተኸኝ
የርስትህ ፡ ተካፋይ ፡ የአንተው ፡ አደረከኝ
ለዚህ ፡ ልታበቃኝ ፡ ታዲያ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ (፪x)

አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x)

ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)
አመሰግንሃለው (፮x)

ማዕበሉ ፡ በዝቶብኝ ፡ እኔን ፡ ሲያንገላታኝ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አልኩኝ ፡ ሥምህን ፡ ጠራሁኝ
እጅህን ፡ ዘርግተህ ፡ በፀናችው ፡ ክንድህ
ታደከኝ ፡ አዳንከኝ ፡ ተባረክ ፡ ልበልህ (፪x)

አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x)

ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)
አመሰግንሃለው (፮x)

የተገለጠውን ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ
እንዳልተቀበለ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ
ምህረት ፡ ማዳንህን ፡ ሁሌ ፡ አወራለሁ
አምላኬ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ፍፁም ፡ አምላክ ፡ ማነው (፪x)

አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x)

ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)
አመሰግንሃለው (፮x)

በለቅሶ ፡ ሸለቆ ፡ በወሰንከው ፡ ስፍራ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ በረከትህ ፡ በዛ
ከኃይል ፡ ወደ ፡ ኃይል ፡ ያሸጋገርከኝ
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነልኝ ፡ ኧረ ፡ ምን ፡ ጐደለኝ (፪x)

አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x)

ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)
አመሰግንሃለው (፮x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue