የጠላትህን ፡ ክስ ፡ ሊደመስስልህ
ከዓብ ፡ ዘንድ ፡ የቆመ ፡ ጠበቃ ፡ አለልህ
የኃጢአትህን ፡ ሸክም ፡ ተናዘህ ፡ እረፈው
በደሙ ፡ ያጥበዋል ፡ ለኢየሱስ ፡ ንገረው
አዝ፦ ደስ ፡ ይበልህ ፡ ወንድሜ ፡ ከሳሽህ ፡ ተጥሏል
የኃጢአትህ ፡ ዋጋ ፡ በጌታ ፡ ተከፍሏል
ምህረቱን ፡ ተቀበል ፡ ኃዘንህን ፡ እርሳው
ከንስሐ ፡ ወዲያ ፡ ልብህን ፡ ደስታ ፡ ይሙላው
በእድፋሙ ፡ ልብስህ ፡ ሰውነትህ ፡ ተከድኖ
በአፍረት ፡ ተውጠህ ፡ በደልህ ፡ ተጋኖ
ምንም ፡ ነገር ፡ ቢሆን ፡ "ከቶ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥም"
ብለህ ፡ ተሟገተው ፡ "ከፀጋው ፡ አልሸሽም"
አዝ፦ ደስ ፡ ይበልህ ፡ ወንድሜ ፡ ከሳሽህ ፡ ተጥሏል
የኃጢአትህ ፡ ዋጋ ፡ በጌታ ፡ ተከፍሏል
ምህረቱን ፡ ተቀበል ፡ ኃዘንህን ፡ እርሳው
ከንስሐ ፡ ወዲያ ፡ ልብህን ፡ ደስታ ፡ ይሙላው
ጠላትህን ፡ ጥሎ ፡ እስራትህን ፡ ቆርጦ
ክስህን ፡ ደምስሶ ፡ ፍርድህን ፡ ለውጦ
ያ ፡ የፍቅር ፡ አምላክ ፡ ምህረትን ፡ አውጇል
ልብስህም ፡ እንዲቀየር ፡ ትዕዛዝን ፡ አውጥቷል
አዝ፦ ደስ ፡ ይበልህ ፡ ወንድሜ ፡ ከሳሽህ ፡ ተጥሏል
የሃጥያትህ ፡ ዋጋ ፡ በጌታ ፡ ተከፍሏል
ምህረትን ፡ ተቀበል ፡ ሃዘንህን ፡ እርሳ
ከንስሃ ፡ ወዲያ ፡ ልብህን ፡ ደስታ ፡ ይሙላው