• 165
  • 0
  • 0
  • 0
  • 0

Endeniema Bihon (እንደ ፡ እኔማ ፡ ቢሆን )

እንደኔማ ፡ ቢሆን ፡ አልቆልኝ ፡ ነበረ
የበደሌ ፡ ብዛት ፡ እየተቆጠረ
ጌታዬ ፡ ግን ፡ አምላኬ ፡ ግን ፡ ዕዳዬን ፡ አስቀረ (፪x)

በዘለዓለም ፡ ሥሙ ፡ ቃልኪዳን ፡ ገባልኝ
አንቺ ፡ ልጅ ፡ በሕይወት ፡ ትኖሪያለሽ ፡ አለኝ
ጌታዬ ፡ ነው ፡ አዳኜ ፡ ነው ፡ እኔ ፡ እወደዋለሁ (፪x)

የኃጥያቴ ፡ ቀንበር ፡ ከብዶ ፡ እያስጨነቀኝ
ከሰው ፡ ሁሉ ፡ መሃል ፡ ነጥሎ ፡ እያስቀረኝ
ጌታዬ ፡ ግን ፡ አምላኬ ፡ ግን ፡ ፈልጐ ፡ አገኘኝ (፪x)

ያደረኩትን ፡ ሁሉ ፡ የልቤን ፡ ነገረኝ
ኃጥያቴን ፡ ሻረና ፡ ከሰው ፡ ቀላቀለኝ
አምላኬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ነው ፡ እኔ ፡ አመልከዋለሁ (፪x)

ዳግም ፡ ላልጠማ ፡ ቀንበር ፡ ላይጫነኝ
ከጨለማው ፡ ሰፈር ፡ ጠርቶ ፡ አወጣኝ
ጌታዬ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ እኔ ፡ አመልከዋለሁ (፪x)

ዝም ፡ በይ ፡ አትበሉኝ ፡ እኔ ፡ ዝም ፡ አልልም
የተረደገልኝ ፡ ዝም ፡ አያሰኘኝም
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ የደረሰው
ጌታዬ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ እገዛለታለሁ

Baru-baru ini Didengarkan oleh

0 komentar
    Tidak ada komentar yang ditemukan

:: / ::
::
/ ::

Antre