ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር (Yehie New Egziabhier)

አዝ፦ ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ የደረሰው
ከጠበኩት ፡ በላይ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው
ስለዚህ ፡ በፊቱ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ
ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ (፪x)

ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ሰጣለሁ
ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ አበዛለሁ (፪x)

ፀሐይ ፡ ምትወጣ ፡ በስተምስራቅ ፡ በኩል
ሲመሽባት ፡ ደግሞ ፡ በስተምዕራብ ፡ ብትሆን
ማንም ፡ አይገረምም ፡ በነዚህ ፡ ድርጊቷ
ወግና ፡ ስርአቷ ፡ ልክ ፡ ከጥንት ፡ ፍጥረቷ
አንድ ፡ ቀን ፡ በደቡብ ፡ ብትወጣ ፡ በድንገት
ሲመሽባት ፡ ደግሞ ፡ ሰሜንን ፡ ብትመርጥ
ያኔ ፡ እንግዳ ፡ ነገር ፡ ለሁሉም ፡ ይሆናል
ለእኔ ፡ ግን ፡ አምላኬ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ አድርጓል

ጉድ ፡ ተባለ ፡ ሆኖ ፡ ያልተጠበቀ
ተሰራልኝ ፡ በዓለም ፡ ያልታወቀ
እርሱ ፡ ሚለው ፡ የመዳኔ ፡ ነገር
ከሞት ፡ የመትረፌ ፡ አያልቅም ፡ ቢነገር (፬x)

አዝ፦ ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ የደረሰው
ከጠበኩት ፡ በላይ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው
ስለዚህ ፡ በፊቱ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ
ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ

ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ሰጣለሁ
ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ አበዛለሁ (፪x)

እንዲህ ፡ በቀላሉ ፡ እንደዋዛ ፡ ታልፎ
ሊተው ፡ አይቻልም ፡ አያስቀምጥ ፡ አርፎ
ውስጡ ፡ የተቀመጠው ፡ ምህረቱ ፡ የገባው
ይነዘንዘዋል ፡ ቀን ፡ ከሌት ፡ ውለታው
ቢያቅተኝ ፡ ቢቸግረኝ ፡ ዝም ፡ ማለት
ጉባኤ ፡ መጣሁኝ ፡ ሕዝቡ ፡ ባለበት
እኔ ፡ እያስታወስኩኝ ፡ ያረገውን ፡ ስራ
አምልኮን ፡ ልሰዋ ፡ ከጉባኤው ፡ ጋራ

የገባው ፡ ሰው ፡ የተደረገለት
ያላስቻለው ፡ ውለታው ፡ ያለበት
ይነሳና ፡ አብሮኝ ፡ ከፍ ፡ ያድርገው
ምህረትና ፡ ፍቅር ፡ እሰከ ፡ ዘለዓለም ፡ ነው (፬x)

አዝ፦ ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ የደረሰው
ከጠበኩት ፡ በላይ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው
ስለዚህ ፡ በፊቱ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ
ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ

ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ሰጣለሁ
ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ አበዛለሁ (፪x)

በመስቀል ፡ ላይ ፡ ለእኔ ፡ የሰራውን ፡ ስራ
ቀንም ፡ ሆነ ፡ ሌሊት ፡ ሁልጊዜ ፡ ባወራ
ቃላት ፡ አይበቃኝም ፡ ዓረፍተ ፡ ነገሮች
እንጂ ፡ የእርሱ ፡ ስራ ፡ አያልቅም ፡ እንደ ፡ ሌሎች
ዕልልታና ፡ አምልኮ ፡ ላምላኬ ፡ ሳላስቀር
በምሥጋና ፡ ፊቱ ፡ ከመቅረብ ፡ በስተቀር
ሌላ ፡ ምን ፡ ምርጫ ፡ አለኝ ፡ ለእርሱ ፡ የምሰጠው
ገና ፡ ጨማምሬ ፡ ምሥጋና ፡ እሰዋለሁ

መቼ ፡ ያልቃል ፡ ቢወራ ፡ ቢወራ
ተናግሬ ፡ መቼም ፡ አያበቃ
እርሱም ፡ ቢሆን ፡ የመዳኔ ፡ ነገር
የመስቀሉ ፡ ስራ ፡ አያልቅም ፡ ቢነገር (፬x)
የኢየሱስ ፡ ስራ ፡ አያልቅም ፡ ቢነገር (፪x)

አዝ፦ ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ የደረሰው
ከጠበኩት ፡ በላይ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው
ስለዚህ ፡ በፊቱ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ
ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ

ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ሰጣለሁ
ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ አበዛለሁ (፪x)

"ጸሎት ፡ ሰዓት"

አዝ፦ አተገመትም ፡ በሊቃናት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት
አትገመትም ፡ በሺ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x)

የችግር ፡ ቋጠሮ ፡ ውስብስብ ፡ ሲልብህ
መግቢያ ፡ መውጫ ፡ ጠፍቶህ ፡ ግራ ፡ ሲያጋባህ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ
ደግሞ ፡ ሲፈታታ ፡ ችግር ፡ ሁሉ ፡ ሲተን
የትላንት ፡ ጨለማ ፡ እንደጉም ፡ ሲበተን
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ

አዝ፦ አተገመትም ፡ በሊቃናት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት
አትገመትም ፡ በሺ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x)

አንተን ፡ እንዳላመልክ ፡ ከፍታው ፡ ዝቅታ
ከቶ ፡ አያግደኝም ፡ አይጠፋኝ ፡ ዕልልታ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ
ውስጤ ፡ ቅኔ ፡ ሞልቷል ፡ ከገጠመኝ ፡ በላይ
አምላኬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህና ፡ ኤልሻዳይ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ

አዝ፦ አተገመትም ፡ በሊቃናት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት
አትገመትም ፡ በሺ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x)

ሁሉም ፡ ነገር ፡ ጠፍቶ ፡ በቤቴ ፡ የሚበላ
ያልጠበኩት ፡ ነገር ፡ ሲሆንብኝ ፡ ሌላ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ
ደግሞ ፡ በጐጆዬ ፡ በረከት ፡ ሲሞላ
ሁሉም ፡ ነገር ፡ ሞልቶ ፡ ሲተርፈኝ ፡ ለሌላ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ

አዝ፦ አተገመትም ፡ በሊቃናት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት
አትገመትም ፡ በሺ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x)

ሲሞላ ፡ ዘምሬ ፡ ሲጐድል ፡ ላላለቅስ
በምንም ፡ ሁኔታ ፡ አምልኮ ፡ አልቀንስም
አንተ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ነህ
እታመንሃለሁ ፡ በምሥጋና ፡ ሆኜ
ድል ፡ እንደምትሰጠኝ ፡ በስምህ ፡ አምኜ
አንተ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ነህ

አዝ፦ አተገመትም ፡ በሊቃናት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት
አትገመትም ፡ በሺ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

በተመጣጣኝ በጀት እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads:: / ::
::
/ ::

Queue