Endalkachew Hawaz--Egzabher Tilk New--ነፍሴ ፡ ጠዋት ፡ ማታ

ታስተማምናለህ ፡ ጌታዬ ፡ እኔም ፡ ታመንኩብህ
ታስተማምናለህ ፡ ብቻህን ፡ እኔን ፡ ተደገፍኩብህ (፪x)
ታምኜብሃለሁ ፡ ተደግፌሃለሁ
ዘመኔን ፡ በሙሉ ፡ በአንተ ፡ እመካለሁ (፪x)

አዝ፦ ነፍሴ ፡ ጠዋት ፡ ማታ ፡ አንተን ፡ ታከብራለች
በቀን ፡ በሌሊትም ፡ ትባርክሃለች (፪x)
የመኖሬ ፡ ትርጉም ፡ የሕይወቴ ፡ መሰረት
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ የጸናሁብህ ፡ አለት (፪x)

ለምን ፡ እንደምኖር ፡ አውቃለሁ ፡ አንተን ፡ ስላገኘሁ
ለሕይወቴ ፡ ትርጉምን ፡ ሰጥተሃል ፡ ልቤን ፡ አሳርፈሃል
አርፌብሃለሁ ፡ ረክቼብሃለሁ
ከቤትህ ፡ ጠል ፡ ጠጥቼ ፡ እኔስ ፡ እፎይ ፡ ብያለሁ (፪x)

እግሮቼ ፡ በዓለት ፡ ላይ ፡ ቆመዋል
እኔ ፡ አልናወጥም
አረማመዴም ፡ ጸንቶልናል ፡ መሰረቴ ፡ አይወድቅም
የማዕዘን ፡ ድንጋይ ፡ የሕይወቴ ፡ እራስ
ብቃቴም ፡ ጉልበቴም ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ (፪x)

አዝ፦ ነፍሴ ፡ ጠዋት ፡ ማታ ፡ አንተን ፡ ታከብራለች
በቀን ፡ በሌሊትም ፡ ትባርክሃለች (፪x)
የመኖሬ ፡ ትርጉም ፡ የሕይወቴ ፡ መሰረት
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ የጸናሁብህ ፡ አለት (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue