አዝ፦ እርስ ፡ በእርሳችሁ ፡ በአንድ ፡ ሃሳብ ፡ ተስማሙ
የትዕቢትን ፡ ነገር ፡ አታስቡ (፬x)
ግቅራቹህ ፡ ያለግብዝነት ፡ ይሁን
ክፉውን ፡ ነገር ፡ ተጸየፉ
ከበጐ ፡ ነገር ፡ ጋር ፡ ተባበሩ
በወንድማማች ፡ መዋደድ ፡ ተዋደዱ
አዝ፦ እርስ ፡ በእርሳችሁ ፡ በአንድ ፡ ሃሳብ ፡ ተስማሙ
የትዕቢትን ፡ ነገር ፡ አታስቡ (፪x)
እርስ ፡ በእርሳቹህ ፡ ተከባበሩ
ለስራ ፡ ከመትጋት ፡ አትለግሙ
በመንፈስ ፡ ግምት ፡ እንኳን ፡ ጥሩ ፡ ሁኑ
ደግሞም ፡ ለጌታ ፡ ተገዙ
አዝ፦ እርስ ፡ በእርሳችሁ ፡ በአንድ ፡ ሃሳብ ፡ ተስማሙ
የትዕቢትን ፡ ነገር ፡ አታስቡ (፪x)
በተስፋም ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይበላቹህ
በመከራቹህ ፡ ሁሉ ፡ ታገሱ
በጸሎትም ፡ ሁሉ ፡ ደግሞ ፡ ጽኑ
ቅዱሳንን ፡ በሚያስፈልጋቸው ፡ እርዱ
አዝ፦ እርስ ፡ በእርሳችሁ ፡ በአንድ ፡ ሃሳብ ፡ ተስማሙ
የትዕቢትን ፡ ነገር ፡ አታስቡ (፪x)