ፀሐይ ፡ አትጠልቅም (Tsehay Atetelqem) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

ያየሁትን ፡ አይቼ (ኧረ ፡ እንዴት)
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ልመለስ ፡ ፈርቼ (ያየሁትን)
ያየሁትን ፡ አይቼ (ኧረ ፡ እንዴት)
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ልመለስ ፡ ፈርቼ (፪x)

ሰምቼ ፡ ወጥቻለሁ ፡ የተናገረኝን
መሃል ፡ ላይ ፡ ደርሼ ፡ ግራ ፡ አይገባኝም
ሰምቼ ፡ ወጥቻለሁ ፡ የተናገረኝን
ዮርዳኖስ ፡ ቢሞላ ፡ ግራ ፡ አይገባኝም

የተናገረኝ ፡ ያለኝን ፡ ሳላይ
ፀሐይ ፡ አትጠልቅም ፡ ከቶ ፡ በእኔ ፡ ላይ (፪x)
(እሰይ)

ጭንገፋ ፡ በዘመኔ ፡ በእኔ ፡ እንዳይሰራ
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ቆሟል ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x)
በእኔ ፡ የተጀመረው ፡ ሥራ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
የሚያስተጓጉለኝ ፡ እርሱ ፡ የትኛው ፡ ነው
በእኔ ፡ የተጀመረው ፡ ሥራ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
የሚያስተጓጉለኝ ፡ እርሱ ፡ የትኛው ፡ ነው

ሰው ፡ አይደለም ፡ የተናገረኝ
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ትወርሻለሽ ፡ ያለኝ
ሰው ፡ አይደለም ፡ የተናገረኝ
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ትወርሳለህ ፡ ያለኝ (፪x)

ተናግሮ ፡ ማድረግ (ጌታ) ፡ ጌታ ፡ ከቻለ (አሜን)
ልቤ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ዛሬም ፡ ታመነ (ተናግሮ)
ተናግሮ ፡ ማድረግ (እርሱ) ፡ ጌታ ፡ ከቻለ (አሃሃ)
ልቤ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ዛሬም ፡ ታመነ

ከአፉ ፡ ቃል ፡ በቀር ፡ ከተናገረው
በእኔ ፡ ላይ ፡ አይሆንም/አይሰራም ፡ ጠላቴ ፡ ያለው (፬x)

ይጨምር ፡ እሳቱ ፡ ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ቢነድ
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ በዚያ ፡ አለው ፡ መንገድ (፫x)

የተናገረኝ
(ያለኝን ፡ ሳላይ) ፡ ያለኝን ፡ ሳላይ
(ፀሐይ ፡ አትጠልቅም) ፡ ፀሐይ ፡ አትጠልቅም
(ከቶ ፡ በእኔ ፡ ላይ) ከቶ ፡ በእኔ ፡ ላይ (፪x)

በጨለማው ፡ ላይ ፡ ብርሃን ፡ ይብራ ፡ ያለው
እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ብርሃን ፡ ነው (፬x)
በጨለማው ፡ ላይ ፡ ብርሃን ፡ ይብራ ፡ ያለው
እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ብርሃን ፡ ነው (፬x)

የተናገረኝ
(ያለኝን ፡ ሳላይ) ፡ ያለኝን ፡ ሳላይ
(ፀሐይ ፡ አትጠልቅም) ፡ ፀሐይ ፡ አትጠልቅም
(ከቶ ፡ በእኔ ፡ ላይ) ከቶ ፡ በእኔ ፡ ላይ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue