አዝ፦ በደመና ፡ ይመለሳል
በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል
ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል (፪x)
አባት ፡ እንደሌለው ፡ አልተዋችሁም
ስፍራን ፡ ላዘጋጅ ፡ እንጂ ፡ እንድወስዳቹህ
ልባቹን ፡ አይፍራ ፡ በእኔ ፡ እመኑ
ቶሎ ፡ እመልሳለሁ ፡ ልወስዳቹህ
አዝ፦ በደመና ፡ ይመለሳል
በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል
ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል (፪x)
እንኳን ፡ መኖሪያችን ፡ ቤታችን
ሊፈርስ ፡ ተስፋ ፡ ቢያጣ ፡ ኑሯችን
በእጅ ፡ ያልተሰራ ፡ ጌታ ፡ ያዘጋጃል
ተስፋችን ፡ ላይኛይቱ ፡ ጽዮን ፡ ናት
አዝ፦ በደመና ፡ ይመለሳል
በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል
ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል (፪x)
በዚህ ፡ ዓለም ፡ ኑሯችን ፡ ያበቃል
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሊወስደን ፡ ይመጣል
ብርሃን ፡ በሞላባት ፡ ቅድስት ፡ ሃገር
ጊዜው ፡ ደርሷል ፡ እንሂድ ፡ እንዘምር
አዝ፦ በደመና ፡ ይመለሳል
በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል
ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል (፪x)