አዋቂ ፡ ነህ (Awaqi Neh) - ናዝሬት ፡ አማኑኤል ፡ ሽብሸባ ፡ መዘምራን

ትልቁ ፡ ጌታዬ ፡ ኤሄሄ፡ ትልቁ ፡ አምላኬ ፡ ኤሄሄ ፡ ትልቁ ፡ ጌታዬ ፡ ኤሄሄ
ማን ፡ እንደአንተ ፡ ለእኔ ፡ እንስከዛሬ (፬x)
ትልቁ ፡ ጌታዬ ፡ ትልቁ ፡ አምላኬ ፡ ትልቁ ፡ ጌታዬ
ማን ፡ እንደአንተ ፡ ለእኔ ፡ እንስከዛሬ (፬x)
እንተን ፡ እንዳላስተያይ ፡ ከሌላ ፡ ነውር ፡ ሆነብኝ (፬x)

ከማንስ ፡ ጋር ፡ ላወዳድርህ ፡ ከማንስ ፡ ጋር ፡ ላመሳስልህ
ከማንስ ፡ ጋር ፡ ላወዳድርህ ፡ ከማንስ ፡ ጋር ፡ ላመሳስልህ
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ እህህ
ከአእምሮዪ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ እህህ
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ እህህ
ከአእምሮዪ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ እህህ (፪x)
እንተን ፡ እንዳላስተያይ ፡ ከሌላ ፡ ነውር ፡ ሆነብኝ (፬x)

ዓይኖቼን ፡ ማሳርፍበት ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ የለኝም
ከልቡ ፡ የሚራራልኝ ፡ እንደአንተ ፡ አላገኝም (፪x)

አይነጻጸር ፡ የአንተ ፡ የፍቅር ፡ ቃል
አይወዳደር ፡ የመውደድህ ፡ ጉዳይ
ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ አባቴ ፡ ለእኔ
ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ልበልህ (፪x)

ሰው ፡ መውድዱን ፡ ሲገልጽ ፡ በከንፈሩ ፡ ቃል
አንተ ፡ ግን ፡ ለእኔ ፡ ሞተሃል (፬x)
ሰው ፡ መውድዱን ፡ ሲገልጽ ፡ በከንፈሩ ፡ ቃል
አንተ ፡ ግን ፡ ለእኔ ፡ ሞተሃል (፬x)

አየሁ ፡ በዐይኔ ፡ ስራዬን ፡ ስትሰራ
በዘመኔ ፡ ሆነኸኝ ፡ ከለላ
ረዳት ፡ ሆንከኝ ፡ እኔስ ፡ ታመንኩብህ
እግዚአብሔር ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ (፪x)

አዋቂ ፡ ነህ ፡ አዋቂ ፡ ነህ
አዋቂ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አዋቂ ፡ ነህ (፪x)
" መጽሃፍ ፡ ቅዱስ ፡ ሲናገር ፡ 'አትታበዩ ፡ በኩራትም ፡ አትናገሩ
እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነውና' "
አዋቂ ፡ ነህ ፡ አዋቂ ፡ ነህ
አዋቂ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አዋቂ ፡ ነህ (፪x)
አዋቂ ፡ ነህ ፡ አዋቂ ፡ ነህ
አዋቂ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አዋቂ ፡ ነህ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue