ተመሥገን ፡ ነው ፡ ያለኝ (Temesgen New Yalegn)

ተመስገን ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ለዚህ ፡ ለጌታዬ
እለት ፡ እለት ፡ በዝቷል ፡ ምህረቱ ፡ በላዬ
ተመስገን ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ለዚህ ፡ ለጌታዬ
እለት ፡ እለት ፡ በዝቷል ፡ ምህረቱ ፡ በላዬ

ለዚህ ፡ ሁሉ ፡ ሰላም ፡ ለዚህ ፡ ሁሉ ፡ እረፍት
አንድም ፡ ነገር ፡ የለም ፡ እኔ ፡ የከፈልኩት
የሰጠኸኝ ፡ ሁሉ ፡ ተገብቶኝ ፡ አይደለም
ምህረትህ ፡ በዝቶ ፡ ነው ፡ ክበር ፡ ለዘላላም

ቅዱሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆንህ ፡ ከኔ ፡ ጋራ
ከቅዱሳንም ፡ ጋር ፡ አረከኝ ፡ ምጠራህ
ለዚህ ፡ ያደረሰከኝ ፡ ኧረ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ
ምረትህ ፡ በዝቶ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ክብረልኝ

ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምን ፡ አለ ፡ የሚያስደንቅ ፡ ነገር
አንተ ፡ ከሰው ፡ ጋራ ፡ ከመሆንህ ፡ በቀር
ምታስፈልገውን ፡ አንድም ፡ የሆንከውን
አምላኬ ፡ ተመስገን ፡ አግኝቻለሁ ፡ አንተን

በስምህ ፡ ባሕሩን ፡ ከፍለህ ፡ አሻግረኸኛል
ከጠላትም ፡ ወጥመድ ፡ አስመልጠኸኛል
እዚህ ፡ የደረስኩት ፡ በአንተ ፡ ጥበቃ ፡ ነው
ለበዛው ፡ ምህረትህ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው

Recently Listened by

1 comments
  • Aifanafg 01:30

    netsanet belayneh

     
    1646113710

:: / ::
::
/ ::

Queue