አዝ፦ ደስ ፡ ይለናል ፡ ከአምላካችን ፡ ጋር ፡ ጉዞ
መሄድ ፡ እጁን ፡ ይዞ
መሄድ ፡ እጁን ፡ ይዞ (፪x)
ተራራ ፡ ቁልቁለትም ፡ አቀበትም ፡ ሁሉ ፡ ይስተካከላሉ
ኢየሱስን ፡ እያዩ ፡ ይስተካከላሉ (፪x)
አዝ፦ ደስ ፡ ይለናል ፡ ከአምላካችን ፡ ጋር ፡ ጉዞ
መሄድ ፡ እጁን ፡ ይዞ
መሄድ ፡ እጁን ፡ ይዞ (፪x)
ማዕበልና ፡ ሞገድ ፡ ባሕር ፡ ሲያናውጡን ፡ ፀጥ ፡ ያደርጋቸዋል
ኢየሱስ ፡ ያዛቸዋል ፡ ፀጥ ፡ ያደርጋቸውል (፪x)
አዝ፦ ደስ ፡ ይለናል ፡ ከአምላካችን ፡ ጋር ፡ ጉዞ
መሄድ ፡ እጁን ፡ ይዞ
መሄድ ፡ እጁን ፡ ይዞ (፪x)
ፍቅርን ፡ በተሞላው ፡ አምላክ ፡ ተማምነናል
በመከራ ፡ ስንወድቅ ፡ መቼ ፡ ይተውናል ፡ ነጥቆ ፡ ያወጣናል (፪x)
አዝ፦ ደስ ፡ ይለናል ፡ ከአምላካችን ፡ ጋር ፡ ጉዞ
መሄድ ፡ እጁን ፡ ይዞ
መሄድ ፡ እጁን ፡ ይዞ (፪x)
በጌታ ፡ ክንዶች ፡ ላይ ፡ እንደገፋለን ፡ ስልጣን ፡ በእጁ ፡ ነው
እፎይ ፡ እንላለን ፡ በእርሱ ፡ እንደፍራለን (፪x)
አዝ፦ ደስ ፡ ይለናል ፡ ከአምላካችን ፡ ጋር ፡ ጉዞ
መሄድ ፡ እጁን ፡ ይዞ
መሄድ ፡ እጁን ፡ ይዞ (፪x)