Meserete Kirstos Choir--Endet Dink Amlak New-- Entsenalen (እንፀናለን)

አዝ፦ እንጸናለን ፡ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም
ዛሬን ፡ የጠበቀን ፡ ነገም ፡ አይተወንም
እንጸናለን (፪x)

ዓይናችን ፡ እያየ ፡ ሲንቦለቦል
እውነትስ ፡ ጌታችን ፡ ወዲያ ፡ ካለን
ለጅራፍ ፡ ጀርባችን ፡ እንሰጣለን

አዝ፦ እንጸናለን ፡ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም
ዛሬን ፡ የጠበቀን ፡ ነገም ፡ አይተወንም
እንጸናለን (፪x)

አባቶችን ፡ በእምነት ፡ ያቆመውን
በመጋዝ ፡ መሰንጠቅ ፡ ያጸናውን
ያ ፡ አምላካቸው ፡ ነው ፡ አምላካችን
የሚያጸና ፡ ጉልበት ፡ ታዳጊያችን

አዝ፦ እንጸናለን ፡ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም
ዛሬን ፡ የጠበቀን ፡ ነገም ፡ አይተወንም
እንጸናለን (፪x)

የከንቱ ፡ ቃላቶችን ፡ ደርዳሪ
አንሆንም ፡ በሥጋችን ፡ ቆርቋሪ
መንፈስ ፡ ያስቻለንን ፡ እንቀበል
ተሸክመን ፡ አለን ፡ የእምነት ፡ መሰቀል

አዝ፦ እንጸናለን ፡ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም
ዛሬን ፡ የጠበቀን ፡ ነገም ፡ አይተወንም
እንጸናለን (፪x)

Nedavno slušano od

0 komentari
    Nema komentara

:: / ::
::
/ ::

Red