አዝ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የዘመናት ፡ ንጉሥ
ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ ነው ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ (፪x)
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ አዲስ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ
አይሰለችም ፡ ከቶ ፡ አንተ ፡ እንኳን ፡ ብታምጽ
የመስቀሉ ፡ ቃል ፡ ፈውስ ፡ ነው ፡ ለሕይወት
አምነው ፡ ለተጠጉት ፡ ይሆናል ፡ መሰረት
አዝ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የዘመናት ፡ ንጉሥ
ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ ነው ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ (፪x)
ለሰልፍ ፡ አዘጋጅቶ ፡ ኃይልን ፡ ያስታጥቃል
በላይ ፡ የቆሙትን ፡ ከበታች ፡ ይጥላል
በትንሳኤው ፡ ስልጣን ፡ ውጊያውን ፡ አካሂዶ
ምርኮን ፡ ሰብስብ ፡ አለው ፡ ጠላቱን ፡ አሳዶ
አዝ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የዘመናት ፡ ንጉሥ
ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ ነው ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ (፪x)
ፍላጻን ፡ ወርውሮ ፡ ምሽግን ፡ ነደለ
በአምላኩ ፡ ተማምኖ ፡ ውጊያውን ፡ ቀጠለ
በደም ፡ ጐዳና ፡ ላይ ፡ የኢየሱስ ፡ ነው ፡ ድሉ
ብሎ ፡ ዘምሮለት ፡ ቆመ ፡ በዕጣ ፡ ክፍሉ
አዝ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የዘመናት ፡ ንጉሥ
ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ ነው ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ (፪x)