ፍቅር ፡ ነው

ስለ ፡ ሰው ፡ ልጅ ፡ ነፍሱን ፡ አሳልፎ
እስከ ፡ መስቀል ፡ ታዟል ፡እራሱን ፡ አዋርዶ
እንዲህ ፡ ያለ ፡ መውደድ ፡ ከወዴት ፡ ተሰምቷል?
በእግዚአብሔር ፡ አብ ፡ ፍቃድ ፡ በኢየሱስ ፡ ተገልጧል (፪x)

ፍቅር ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ፍቅር ፡ ነው
ስራው ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ስሙ ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x)

የኃያላን ፡ ጉልበት ፡ ዝናው ፡ ሁሉ ፡ ያልፋል
ክብሩ ፡ ከበሬታው ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ይቀራል
የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ በግርማ ፡ በክብር
በኃይል ፡ በሞገሱ ፡ ፀንቶ ፡ የሚኖር (፪x)

ኃያል ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ኃያል ፡ ነው
ስራው ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ ስሙ ፡ ኃያል ፡ ነው

ፊት ፡ አይቶ ፡ አያደላ ፡ ለሁሉ ፡ ነው ፡ ወዳጅ
የልብ ን ፡ የሚረዳ ፡ እውነተኛ ፡ ፈራጅ
ስራው ፡ በትክክል ፡ ሚዛኑ ፡ እውነት ፡ ነው
በዘመናት ፡ ሁሉ ፡ በስራው ፡ ፃድቅ ፡ ነው (፪x)

ፃድቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ፃድቅ ፡ ነው
ስራው ፡ ፃድቅ ፡ ነው ፡ ስሙ ፡ ፃድቅ ፡ ነው (፪x)

ሌላ ፡ ምን ፡ እንበልህ ፡ ምን ፡ እናቅርብ
በፊትህ ፡ ከማዜም ፡ ከመቀኘት ፡ በቀር (፬x)

ለአንተ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ይኸው ፡ ዝማሬ ፡ አምልኮ
ስግደት ፡ ዕልልታ ፡ ክብር ፡ አሜን ፡ ይሁን (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue