Yegziabher Miretu Bizu (የእግዚአብሔር ፡ ምህረቱ ፡ ብዙ)

የእግዚአብሔር ፡ ምህረቱ ፡ ብዙ
ደካሞችንም ፡ ማገዙ
በጀርባው ፡ አዝሎ ፡ መሸከሙ
ከኃጢአት ፡ ማንጻት ፡ በደሙ (፪x)

አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ለዚህ ፡ ያደረስከኝ ፡ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ (፪x)

እኔስ ፡ አይቻለሁኝ ፡ ፍቅሩን
ከፋንድያ ፡ ላይ ፡ ማንሳቱን
ዛሬ ፡ ሰው ፡ ሆኜ ፡ እዘምራለሁ
ለዚህ ፡ ክብር ፡ በቅቻለሁ (፪x)

አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ለዚህ ፡ ያደረስከኝ ፡ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ (፪x)

እጅግ ፡ ተንቄ ፡ በሰው ፡ ዘንድ
ተጥዬ ፡ ነበር ፡ በአመድ
ግን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ፈልጐኝ
ከኃጢአት/ከጅግር ፡ ማጥ ፡ ውስጥ ፡ አወጣኝ (፪x)

አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ለዚህ ፡ ያደረስከኝ ፡ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ (፪x)

አይገርማችሁም ፡ ወይ ፡ ወገኖች
የልዑል ፡ አምላክ ፡ ባሪያዎች
ተነሱ ፡ ዘምሩ ፡ ለጌታ
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ውለታው (፪x)

አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ለዚህ ፡ ያደረስከኝ ፡ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads



:: / ::
::
/ ::

Queue