ለቅሶ ፡ ማታ ፡ ቢሆንም ፡ ጠዋት ፡ ደስታ ፡ ይሆናል
ሁሉን ፡ ቻዩ ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ ያዛል (፪x)
አዝ:- ቢመሽም ፡ ይነጋል ፡ ይነጋል ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ
እንደጨለመ ፡ አይቀር ፡ አይቀርም ፡ እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ አለው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ አለው ፡ ለሁሉ
እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ አለው (፪x)
አልገፋ ፡ ብሉ ፡ ትላንት ፡ ያስቸገረኝ
ከፊቴ ፡ እየቆመ ፡ አላሳልፍ ፡ ያለኝ
ታሪክን ፡ በታሪክ ፡ በሚሽረው ፡ ጌታ
ሁሉ ፡ ተለወጠ ፡ በቃ ፡ ሲል ፡ አበቃ (፪x)
አያሳፍር ፡ ለተደገፉበት
ይታመናል ፡ ተስፋ ፡ ላረጉበት
መልካም ፡ አምላክ ፡ ሁሌም ፡ ባለፀጋ
እንደርሱ ፡ የለም ፡ ፈጥኖ ፡ የሚረዳ (፪x)
አዝ:- ቢመሽም ፡ ይነጋል ፡ ይነጋል ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ
እንደጨለመ ፡ አይቀር ፡ አይቀርም ፡ እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ አለው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ አለው ፡ ለሁሉ
እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ አለው (፪x)
አንድ ፡ ጊዜ ፡ ቃሉን ፡ ሲሰጥ ፡ ሊሰራ ፡ ሲነሳ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ይለወጣል ፡ ከእርሱ ፡ የተነሳ
እኔም ፡ ይሄ ፡ ገብቶኝ ፡ ተደግፌዋለሁ
በኃያላን ፡ መሃል ፡ ኃይል ፡ የእግዚአብሄር ፡ ነው
በኃያላን ፡ መሃል ፡ ኃይል ፡ የእግዚአብሄር ፡ ነው (፪x)
ኃይል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው (፰x)
ለቅሶ ፡ ማታ ፡ ቢሆንም ፡ ጠዋት ፡ ደስታ ፡ ይሆናል
ሁሉን ፡ ቻዩ ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ ያዛል (፪x)
አዝ:- ቢመሽም ፡ ይነጋል ፡ ይነጋል ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ
እንደጨለመ ፡ አይቀር ፡ አይቀርም ፡ እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ አለው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ አለው ፡ ለሁሉ (እግዚአብሔር)
እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ አለው (፬x)