Betigist Tsetita (በትዕግሥት ፡ ፀጥታ)

አዝ፦ በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ
ድል ፡ ይገኛል ፡ ከጌታ
በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ
መልስ ፡ ይመጣል ፡ ከጌታ

የበረታ ፡ ሰልፍ ፡ ሲከበኝ ፡ ከኋላ ፡ ከፊት
ቆይቼ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ደጅ ፡ ጠናሁት
እርሱም ፡ ዘንበል ፡ አለልኝ ፡ ሊያዳምጠኝ
እንባዬን ፡ በእጁ ፡ ጠርጐ ፡ ቃሉን ፡ ሰጥቶ ፡ አፅናናኝ

አዝ፦ በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ
ድል ፡ ይገኛል ፡ ከጌታ
በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ
መልስ ፡ ይመጣል ፡ ከጌታ

ነፍስህ ፡ ብትራቆት ፡ ፍፁም ፡ ባዶ ፡ ስትሆን
ያለህን ፡ አራግፈህ ፡ ተዘርፈህ ፡ ስታይ ፡ ራስህን
ያሳለፍካቸውን ፡ ድሎች ፡ አስብ ፡ ተስፋህ ፡ ይለምልም
ተንበርክከህ ፡ ብትቆይ ፡ ደግሞ ፡ መዳሰስህ ፡ አይቀርም

አዝ፦ በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ
ድል ፡ ይገኛል ፡ ከጌታ
በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ
መልስ ፡ ይመጣል ፡ ከጌታ

ከድካም ፡ የበረቱ ፡ ሰዎች ፡ በድል ፡ ያለፉ
ከኢየሱስ ፡ በስተቀኝ ፡ በላይ ፡ የተሰለፉ
መንግሥታትን ፡ ድል ፡ ነስተው ፡ ያንን ፡ ምሽግ ፡ የናዱ
የፀሎት ፡ ሰዎች ፡ ናቸው ፡ ጠላት ፡ ያርበተበቱ

አዝ፦ በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ
ድል ፡ ይገኛል ፡ ከጌታ
በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ
መልስ ፡ ይመጣል ፡ ከጌታ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads



:: / ::
::
/ ::

Queue