አዝ፦ ድል ፡ በድል ፡ ጐዳና (፪x)
ክርስቲያን ፡ አሸነፈ ፡ እየሱስ ፡ አለውና (፪x)
ያን ድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ የሞትን ፡ ሸለቆ
ታገለው ፡ ክርስቲያን ፡ የእምነት ፡ ትጥቁን ፡ ታጥቆ
አሻፈረኝ ፡ ብሎ ፡ ለእርሱ ፡ ላይረታ
በድል ፡ ጥሎት ፡ ወጣ ፡ በጌታው ፡ መከታ
አዝ፦ ድል ፡ በድል ፡ ጐዳና (፪x)
ክርስቲያን አሸነፈ ፡ እየሱስ ፡ አለውና (፪x)
የጢሻን ፡ ጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ወጣበት
ክርስቲያን ፡ በእምነት ፡ ሰይፍ ፡ አንዴ ፡ ቢዘምትበት
የማጥመጃ ፡ ሜዳ ፡ በደም ፡ አጥለቅልቆ
ሕያው ፡ ዘር ፡ ዘራበት ፡ እንዲበቅል ፡ አውቆ
አዝ፦ ድል ፡ በድል ፡ ጐዳና (፪x)
ክርስቲያን አሸነፈ ፡ እየሱስ ፡ አለውና (፪x)
ጋሻ ፡ ጦሩን ፡ መንፈስ ፡ ፍላጻው ፡ እምነቱ
ማን ፡ ሊቋቋመው ፡ ነው ፡ ያንን ፡ ክንደ ፡ ብርቱ
ሊያጠምዱት ፡ ቢያስቀሩት ፡ አጥብቀው ፡ ቢጥሩም
ከአምላኩ ፡ ደም ፡ ቅጥር ፡ አልነቀለም ፡ እግሩን
አዝ፦ ድል ፡ በድል ፡ ጐዳና (፪x
ክርስቲያን፡አሸነፈ ፡ እየሱስ ፡ አለውና (፪x)