blessed
ኢየሱስ ፡ ለኔ ፡ ሁሉን ፡ ነው
ጌታዬ ፡ እርሱ ፡ በቂ ፡ ነው
የሚያሻን ፡ የለም ፡ ጌታ ፡ አለኝ
ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ የሆንልኝ
ምን ፡ ያሻኛል ፡ ምን ፡ ያሻኛል ፡ ምን ፡ ያሻኛል
ጌታ ፡ ይበቃኛል
ምን ፡ እሻለሁ ፡ ምን ፡ እሻለሁ ፡ ምን ፡ እሻለሁ
ጌታን ፡ እግኝቻለሁ
የሰማይ ፡ የምድር ፡ ጌታ
በኃይሉ ፡ እጅግ ፡ የበረታ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ የተሰጠኝ
በረከት ፡ ሙላት ፡ የሆንልኝ
ብሩና ፡ ወርቁም ፡ የእርሱ ፡ ነው
አምላኬ ፡ ሁሉን ፡ የፈጠረው
እንደ ፡ ፈቃዱ ፡ የሆነው
የአባቴ ፡ ፈቃድ ፡ ለኔ ፡ ነው
የእርሱ ፡ የሆነው ፡ የእኔ ፡ ነው
ወራሽ ፡ ነኝ ፡ ጌታ ፡ አባቴ ፡ ነው
እንደ ፡ ባሪያ ፡ ሳሆን ፡ እንደ ፡ ልጅ
ተቀብሎኛል ፡ እንደ ፡ ወዳጅ
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እዜማለሁ
በመንፈሥም ፡ እቀኛለሁ
ለእርሱ ፡ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና
ይኸው ፡ መዝሙር ፡ ታላቅ ፡ ነውና
blessed