• 102
  • 0
  • 0
  • 0
  • 0

Getayawqale Girmay--Midir Alefelat ልዑል ፡ ሆይ (Leul Hoy)

አልሰለችም ፡ ፍፁም ፡ ደግሞም ፡ አልታክትም
ምሥጋናን ፡ ከማለት ፡ ከቶ ፡ ዝም ፡ አልልም
ምሕረትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝቶልኝ ፡ ስላየሁ
ተመስገን ፡ እያልኩኝ ፡ ለአንተ ፡ እዘምራለሁ

አዝ፦ ልዑል ፡ ሆይ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x)
ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x)
ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው

ከአዕምሮዬ ፡ በላይ ፡ አድርገህልኛል
እጅህን ፡ ዘርግተህ ፡ ጌታ ፡ ባርከኸኛል
ለዚህ ፡ የምሰጥህ ፡ ምላሽ ፡ ስለሌለኝ
ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ ፡ ለአንተ ፡ ለወደድኸኝ

አዝ፦ ልዑል ፡ ሆይ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x)
ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x)
ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው

ታላቁን ፡ ሥራህን ፡ ማዳንህን ፡ ያዩ
ዘወትር ፡ ሳይታክቱ ፡ ለአንተ ፡ ይቀኛሉ
እኔም ፡ የእጅህን ፡ ሥራ ፡ በዓይኔ ፡ ስላየሁ
ጠዋትና ፡ ማታ ፡ ለክብርህ ፡ እቀኛለሁ

አዝ፦ ልዑል ፡ ሆይ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x)
ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x)
ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው

ምሥጋናን ፡ የሚሠዋ ፡ እርሱ ፡ ያከብረኛል
በማለት ፡ በቃልህ ፡ ጌታ ፡ ተናግረሃል
እኔም ፡ አንተን ፡ ሳከብር ፡ (እጅግ) ደስ ፡ ይለኛል
ይኸው ፡ ፊትህ ፡ ቆምኩኝ ፡ ልሠዋ ፡ ምሥጋና

ምሥጋና ፣ ምሥጋና (፭x)
ይገባዋልና

ዘንድሮ ፡ ምሥጋና ፡ በዛ ፡ በዛ ፡ አሉ
መዝነው ፡ ለክተው ፡ መስጠት ፡ የለመዱ
ግን ፡ ሊበዛ ፡ ቀርቶ ፡ እንደውም ፡ አንሶታል
በእውነትና ፡ መንፈስ ፡ መቼ ፡ ሰጥተውታል
እኔ ፡ ግን ፡ ስሰዋ ፡ ምሥጋናን ፡ ለአምላኬ
ሳልመዝን ፡ ሳልሰፍር ፡ ሰጠሁ ፡ ተንበርክኬ
በእውነትና ፡ መንፈስ ፡ ሳመልከው ፡ አይደክመኝም
ምሥጋናን ፡ ስሰዋ ፡ አይታወቀኝም

ምሥጋና ፣ ምሥጋና (፭x)
ይገባዋልና

በጌታዬ ፡ ካመንኩኝ ፡ ጊዜ ፡ ጀምሮ
ምህረት ፡ ቸርነቱ ፡ አያልቅም ፡ ተነግሮ
ታዲያስ ፡ ካላስቆመ ፡ የእርሱ ፡ በጐነት
ምሥጋናን ፡ እንዴት ፡ ላቁም ፡ በእርሱ ፡ አለኝ ፡ ቸርነት
ብር ፡ ወርቅ ፡ ወይም ፡ አልማዝ ፡ ገንዘብ ፡ ወይም ፡ ዕንቁ
ያረገውን ፡ ውለታ ፡ ስራ ፡ ብቂ
ከምሥጋና ፡ ሌላ ፡ ክፍያ ፡ አይፈልግም
እርሱን ፡ ከማመስገን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ አልልም

ምሥጋና ፣ ምሥጋና (፭x)
ይገባዋልና

ኢየሱስ ፡ ምህረቱን ፡ እያበዛላችሁ
ግን ፡ ምሥጋናን ፡ መስጠት ፡ የደካከማችሁ
ያከብረኛል ፡ ካለ ፡ ምሥጋናን ፡ የሚሰው
የምን ፡ ቁጠባ ፡ ነው ፡ ላታገኘው ፡ ዋጋ
እኔስ ፡ ተነሳብኝ ፡ ምሥጋናን ፡ ተሞላሁ
ቁጠባን ፡ አላቅም ፡ ስለት ፡ ካላስገባሁ
ያውም ፡ ነፍሱን ፡ ሰጥቶኝ ፡ አነሳ ፡ ምሥጋና
ሳመልክ ፡ ላሳያችሁ ፡ ክብሬን ፡ ልጣልና

ምሥጋና ፣ ምሥጋና (፭x)
ይገባዋልና

አዝ፦ ልዑል ፡ ሆይ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x)
ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x)
ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue