Eyerusalem (ኢየሩሳሌም)

አዝ፦ ኢየሩሳሌም ፡ ቅድስቲት ፡ ከተማ
የጐዳናሽ ፡ ውጥንቅጡ ፡ ቢበዛ ፡ እንኳን
ሳላይሽ ፡ አልቀርም ፡ በአምላክ ፡ ኃይል ፡ እርዳታ (፪x)

የናፈቀኝ ፡ ዜማ ፡ የቅዱስ ፡ ዝማሬ (፪x)
አልቀርም ፡ ሳልዘምር ፡ ከጻድቃን ፡ አብሬ
ከበጉ ፡ ዙፋን ፡ ሥር ፡ ሳልዞር ፡ በደስታ (፪x)
አልቀርም ፡ ሳላይሽ ፡ አንች ፡ ቅዱስ ፡ ቦታ

አዝ፦ ኢየሩሳሌም ፡ ቅድስቲት ፡ ከተማ
የጐዳናሽ ፡ ውጥንቅጡ ፡ ቢበዛ ፡ እንኳን
ሳላይሽ ፡ አልቀርም ፡ በአምላክ ፡ ኃይል ፡ እርዳታ (፪x)

ማቋረጫው ፡ መንገድ ፡ ሊጠልፈኝ ፡ ቢነሳ (፪x)
ሳላየው ፡ አልቀርም ፡ የይሁድን ፡ አንበሳ
ብቻዬን ፡ ብቀርም ፡ መንገደኛው ፡ ሸሽቶ (፪x)
ሳልዘምር ፡ አልቀርም ፡ ኢየሱሴ ፡ መጥቶ

አዝ፦ ኢየሩሳሌም ፡ ቅድስቲት ፡ ከተማ
የጐዳናሽ ፡ ውጥንቅጡ ፡ ቢበዛ ፡ እንኳን
ሳላይሽ ፡ አልቀርም ፡ በአምላክ ፡ ኃይል ፡ እርዳታ (፪x)

የመናይ ፡ ተራራ ፡ መቧጠጥ ፡ ቢያቅተኝ (፪x)
የበረሃው ፡ ጉዞ ፡ ውኃ ፡ ጥም ፡ ቢጐዳኝ
የሚያረካው ፡ ጉዞ ፡ ሲመታ ፡ ከሰማይ (፪x)
ይረዳኛል ፡ በርግጥ ፡ ያቺን ፡ ቦታ ፡ እንዳይ

አዝ፦ ኢየሩሳሌም ፡ ቅድስቲት ፡ ከተማ
የጐዳናሽ ፡ ውጥንቅጡ ፡ ቢበዛ ፡ እንኳን
ሳላይሽ ፡ አልቀርም ፡ በአምላክ ፡ ኃይል ፡ እርዳታ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue