Rohobot (ርሆቦት)

እስከሚያውቁኝ ፡ የተጣሉኝ ፡ ሁሉ
አስፍቶኛል ፡ ጌታ ፡ እንደ ፡ ቃሉ
እኔም ፡ በዝቻለሁ ፡ ደስ ፡ ብሎኛል
ፍሬዬም ፡ አብቦ ፡ ይሄው ፡ ይታያል

እንዲያ ፡ ያሳደዱኝ ፡ ጠላቶቼ
ለመሆን ፡ ፈለጉ ፡ ወዳጆቼ
እርሆቦት ፡ ጌታ ፡ ስላሰኘኝ
እግዚአብሔር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ አለኝ

አዝ፦ ሮሆቦት (፪x) ፡ እግዚአብሔር ፡ አስፍቶልኛል
መሻቴንም ፡ ፈጽሞልኛል (፪x)

የገባልኝን ፡ ቃል ፡ እይፈጽምም
ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ከቶ ፡ አይሆንም
ባልኩኝ ፡ ጊዜ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል
ርሆቦት ፡ ጌታ ፡ አስፍቶልኛል

ዛሬ ፡ አቁሞኛል ፡ በተራራ
አሳልፎ ፡ ያንን ፡ ሁሉ ፡ መከራ
እኔም ፡ እነግራለሁ ፡ በረከቴን
ያደረገልኝን ፡ መድሃኔቴን

አዝ፦ ሮሆቦት (፪x) ፡ እግዚአብሔር ፡ አስፍቶልኛል
መሻቴንም ፡ ፈጽሞልኛል (፪x)

አሁን ፡ ግን ፡ ጽዋዬ ፡ ተርፎልኛል
እስክረሰርስ ፡ ድረስ ፡ ሞልቶልኛል
ከእንግዲህ ፡ በኋላ ፡ ከቶ ፡ አልጐድልም
በረከት ፡ አድርጐኛል ፡ ለዚህ ፡ ዓለም

የገባልኝን ፡ ቃል ፡ አይፈጽምም
ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ከቶ ፡ አይሆንም
ባልኩኝ ፡ ጊዜ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል
ርሆቦት ፡ ጌታ ፡ አስፍቶልኛል

አዝ፦ ሮሆቦት (፪x) ፡ እግዚአብሔር ፡ አስፍቶልኛል
መሻቴንም ፡ ፈጽሞልኛል (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue