Ejun Zergito (እጁን ፡ ዘርግቶ)

የሞትንስ ፡ ፍርድ ፡ ብዙ ፡ ጊዜ ፡ ሰምተናል
በሕይወት ፡ ለመኖር ፡ ዕለት ፡ ዕለት ፡ ሞተናል
የኢየሱስን ፡ ሞት ፡ ተሸክመን ፡ ዞረናል
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ በምህረቱ ፡ ኖረናል

አዝ፦ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ጌታ ፡ ባይረዳን ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ሆኖ
በችግራችን ፡ ባይታደገን ፡ እንደዚህ ፡ ፈጥኖ
ረግረጉ ፡ ውጦን ፡ ልንጠፋ ፡ ነበር ፡ ውኃ ፡ አስጥሞን
ዛሬ ፡ ግን ፡ ድነን ፡ በሕይወት ፡ አለን ፡ ኢየሱስ ፡ አውጥቶን

በእምነት ፡ እንጂ ፡ በምናየው ፡ አይደለም
ከጌታ ፡ በቀር ፡ እኛ ፡ ትምክህት ፡ የለንም
ጽድቃችን ፡ እንኳን ፡ ለዚህ ፡ አላበቃንም
ፀጋው ፡ አጽንቶን ፡ ከርሱ ፡ አልተለየንም

አዝ፦ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ጌታ ፡ ባይረዳን ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ሆኖ
በችግራችን ፡ ባይታደገን ፡ እንደዚህ ፡ ፈጥኖ
ረግረጉ ፡ ውጦን ፡ ልንጠፋ ፡ ነበር ፡ ውኃ ፡ አስጥሞን
ዛሬ ፡ ግን ፡ ድነን ፡ በሕይወት ፡ አለን ፡ ኢየሱስ ፡ አውጥቶን

ሕያዋን ፡ ሆነን ፡ በእርሱ ፡ እንኖራለን
የጌታን ፡ ሥራ ፡ ዛሬም ፡ እንገልጻለን
ክብር ፡ ለሥሙ ፡ ሞገስ ፡ ለሥሙ ፡ ብለን
ያለንን ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ እንሰዋለን

አዝ፦ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ጌታ ፡ ባይረዳን ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ሆኖ
በችግራችን ፡ ባይታደገን ፡ እንደዚህ ፡ ፈጥኖ
ረግረጉ ፡ ውጦን ፡ ልንጠፋ ፡ ነበር ፡ ውኃ ፡ አስጥሞን
ዛሬ ፡ ግን ፡ ድነን ፡ በሕይወት ፡ አለን ፡ ኢየሱስ ፡ አውጥቶን

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads

:: / ::
::
/ ::

Queue