Keber Lehonen Gieta (ክብር ፡ ለሆነን ፡ ጌታ)

ክበር ፡ የሆነን ፡ ጌታ ፡ ሞገስ ፡ የሆነን ፡ ጌታ
ብቃት ፡ የሆነን ፡ ጌታ ፡ በጉድለታችን ፡ ፈንታ
ክንዱን ፡ በዘመናችን ፡ በዓይናችን ፡ አይተነዋል
መልካም ፡ እረኛ ፡ ኢየሱስ ፡ እስከዛሬ ፡ ረድቶናል

በዘመን ፡ በአመታት ፡ መሃል ፡ የሚገዳደረው ፡ የታል
ብቻውን ፡ ድንቅ ፡ እየሰራ ፡ የሚኖር ፡ እንደተፈራ
ለእኛም ፡ ይሄው ፡ ሞገስ ፡ ሆነን ፡ ባሕሩን ፡ ከፍሎ ፡ አሻገረን
ችግራችንን ፡ እረሳነው ፡ በኢየሱስ ፡ ስንቱን ፡ አለፍን

አዝ
ክበር ፡ የሆነን ፡ ጌታ

ስንቱን ፡ ተሻገርን ፡ አለፍን ፡ በምሥጋና ፡ ሆ ፡ እያልን
ስንቱስ ፡ ከእግራችን ፡ ወደቀ ፡ በኢየሱስ ፡ እየደቀቀ
ዘመን ፡ ሲያልፍ ፡ ዘመን ፡ ሲተካ ፡ ፍሬያችን ፡ አብቦ ፡ ፈካ
የረገጥነውን ፡ ወረስን ፡ እለት ፡ እለት ፡ አማረብን

አዝ
ሞገስ ፡ የሆነን ፡ ጌታ

በምድረ ፡ በዳ ፡ በረሃ ፡ የሚያረካ ፡ ውኃ ፡ ሆነን
አልሰለቸን ፡ የእኛ ፡ ጌታ ፡ እንደቃሉ ፡ ተለመነን
በመከራ ፡ ቀን ፡ ሰቀቀን ፡ ተማምነን ፡ ስሙን ፡ ስንጠራ
ደረሰልን ፡ በሰአቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ የሚያኮራ

አዝ
ክብር ፡ የሆነን ፡ ጌታ

ሸንጐ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ሲማከር ፡ ዲያብሎስ ፡ ሊያጠፋን ፡ ሲጥር
ማነው ፡ ደርሶ ፡ የታደገን : በመከራ : መርከብ ፡ ሆነን
ታሪክ ፡ ይናገር ፡ ብዙ ፡ ነው : ብዙ ፡ ነው ፡ እኛስ ፡ ያለፍነው
ከእግራችን ፡ ስር ፡ ወድቆ ፡ ጠላት ፡ ጭንቅላቱን ፡ ረገጥነው

አዝ
ክበር ፡ የሆነን ፡ ጌታ

האזינו לאחרונה על ידי

0 הערות
    לא נמצאו הערות

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast
Buy Me a Coffee Button Buy Wongelnet a Coffee

If you appreciate the work we do at Wongelnet and would like to support our ongoing development, research, and the efforts of our support staff, we’d be incredibly grateful if you could buy us a coffee.

Your support not only helps us keep the lights on but also fuels our passion to continue improving the platform and providing you with the best possible service. Every little bit helps us stay focused on delivering the features and updates that matter most to you.


Thank you for being a part of our journey!
You can now buy us a coffee! You can now buy us a coffee

Advertise Here



:: / ::
::
/ ::

תוֹר