አመታት ፡ አይለውጡህ (Ametat Aylewetuhem)

አመታት ፡ አመታት ፡ አንተን ፡ አይለውጡህም (፪x)
ዘመናት ፡ ዘመናት ፡ አንተን ፡ አይለውጡህም (፪x)

ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ለዘላለም
አምረህ ፡ ደምቀህ ፡ አሸብርቀህ
በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ትኖራለህ
አምረህ ፡ ደምቀህ ፡ አሸብርቀህ
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አላረጀህ
አምረህ ፡ ደምቀህ ፡ አሸብርቀህ
የይስሃቅ ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አላረጀህ
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አላረጀህ

ስንቶቹ ፡ ነገሥታቶች ፡ ሲያልፉ ፡ ሲሻሩ
የእኛ ፡ አምላክ ፡ ብቻውን ፡ አለ ፡ በክብሩ
የነገሥታቶች ፡ ንጉሥ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ
አይደክመው ፡ አይታክተው ፡ ሁሉን ፡ ሊረታ

አመታት ፡ አመታት ፡ አንተን ፡ አይለውጡህም (፪x)
ዘመናት ፡ ዘመናት ፡ አንተን ፡ አይለውጡህም (፪x)

ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ለዘላለም
አምረህ ፡ ደምቀህ ፡ አሸብርቀህ
በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ትኖራለህ
አምረህ ፡ ደምቀህ ፡ አሸብርቀህ ፡
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አላረጀህ
አምረህ ፡ ደምቀህ ፡ አሸብርቀህ
የይስሃቅ ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አላረጀህ
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አላረጀህ

በእነ ፡ አብርሃም ፡ ዘመን ፡ የነበረው
ሕዝቡን ፡ በምድረ ፡ በዳ ፡ የሚመራው
የዳዊት ፡ የሙሴ ፡ አምላክ ፡ መች ፡ ደከመው
የቀን ፡ የወሩ ፡ ብዛት ፡ አልለወጠው

አመታት ፡ አመታት ፡ አንተን ፡ አይለውጡህም (፪x)
ዘመናት ፡ ዘመናት ፡ አንተን ፡ አይለውጡህም (፪x)

ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ለዘላለም
አምረህ ፡ ደምቀህ ፡ አሸብርቀህ
በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ትኖራለህ
አምረህ ፡ ደምቀህ ፡ አሸብርቀህ
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አላረጀህ
አምረህ ፡ ደምቀህ ፡ አሸብርቀህ
የይስሃቅ ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አላረጀህ
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አላረጀህ

በሐዋርያት ፡ ነብያት ፡ ድንቅ ፡ የሰራው
መስራት ፡ አያቅተውም ፡ ዛሬም ፡ ያው ፡ ነው
የአጋንንትን ፡ ምሽግ ፡ ያፈራርሳል
ከጥንቱ ፡ የበለጠ ፡ ዛሬም ፡ ይሰራል

አመታት ፡ አመታት ፡ አንተን ፡ አይለውጡህም (፪x)
ዘመናት ፡ ዘመናት ፡ አንተን ፡ አይለውጡህም (፪x)

ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ለዘላለም
አምረህ ፡ ደምቀህ ፡ አሸብርቀህ
በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ትኖራለህ (፬x)

የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አላረጀህ
የይስሃቅ ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አላረጀህ
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አላረጀህ
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አላረጀህ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue