አቤቱ ፡ ጉልበቴ ፡ ሆይ ፡ እወድሃለሁ (Abietu Gulbetie Hoy Ewedihalehu)

በዙሪያዬ ፡ ሆኖ ፡ ጠላት ፡ ሲያውከኝ
ያሸነፈ ፡ መስሎ ፡ ሲፎክርብኝ
በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ ወዳንተ ፡ ጮህኩኝ
ሰማይን ፡ ዝቅ ፡ አርገህ ፡ ከተፍ ፡ አልክልኝ

አዝ፦ አቤቱ ፡ ጉልበቴ ፡ ሆይ ፡ እወድሃለሁ
አቤቱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ አምባ ፡ መድኃኒቴ
የምታመንበት ፡ ሆነኝ ፡ እረዳቴ (፪x)

እጆቼን ፡ አንስቼ ፡ ተገፋው ፡ አልኩኝ
እግዚአብሔር ፡ ከሰማይ ፡ ተበቀለልኝ
ምድር ፡ ተናወጠች ፡ ቁጣውም ፡ ነደደ
በጠላቶቼ ፡ ላይ ፡ መብረቅ ፡ አወረደ

አዝ፦ አቤቱ ፡ ጉልበቴ ፡ ሆይ ፡ እወድሃለሁ
አቤቱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ አምባ ፡ መድኃኒቴ
የምታመንበት ፡ ሆነኝ ፡ እረዳቴ (፪x)

እግሮቼም ፡ ቆሙልኝ ፡ አልተንሸራተቱም
ጠላቶቼን ፡ ያዝኩኝ ፡ አላመለጡኝም
በኮረብቶቹም ፡ ላይ ፡ ለሚያቆመኝ ፡ ጌታ
እስኪ ፡ ላመስግነው ፡ ልዘምር ፡ በእልልታ

አዝ፦ አቤቱ ፡ ጉልበቴ ፡ ሆይ ፡ እወድሃለሁ
አቤቱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ አምባ ፡ መድኃኒቴ
የምታመንበት ፡ ሆነኝ ፡ እረዳቴ (፪x)

ለሚታመኑበት ፡ እርሱ ፡ ጋሻ ፡ ነው
ክፉዬን ፡ አይወድም ፡ ይነዳል ፡ ቁጣው
ከመቅደሱ ፡ ሆኖ ፡ ድምፄን ፡ ይሰማኛል
እግዚአብሔርን ፡ አይቶ ፡ ጠላቴ ፡ ፈርቶኛል

አዝ፦ አቤቱ ፡ ጉልበቴ ፡ ሆይ ፡ እወድሃለሁ
አቤቱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ አምባ ፡ መድኃኒቴ
የምታመንበት ፡ ሆነኝ ፡ እረዳቴ (፪x)

አቤቱ ፡ ጉልበቴ ፡ ሆይ ፡ እወድሃለሁ
አቤቱ ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ አምባ ፡ መድኃኒቴ
የምታመንበት ፡ ሆነኝ ፡ እረዳቴ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue