Enem Ethiopiawi Nege (እኔም ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ነኝ)

አዝ፦ እኔም ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ነኝ ፡ ብዙ ፡ እንቆቅልሽ ፡ አለኝ
ጌታ ፡ አንተ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ፡ እንቆቅልሽን ፡ መፍታት ፡ ታውቃለህ
የዕውቀት ፡ የጥበብ ፡ ጌታ ፡ እንቆቅልሼን ፡ ፍታ

በዛና ፡ እንቆቅልሼ ፡ ለብዙ ፡ ዘመን ፡ አልቅሼ
አንድ ፡ ቀን ፡ ዝናህን ፡ ሰማሁ ፡ ልነግርህ ፡ ከሳባ ፡ መጣሁ
ተቀመጥ ፡ በዙፋንህ ፡ የልቤን ፡ እንድነግርህ

አዝ፦ እኔም ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ነኝ ፡ ብዙ ፡ እንቆቅልሽ ፡ አለኝ
ጌታ ፡ አንተ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ፡ እንቆቅልሽን ፡ መፍታት ፡ ታውቃለህ
የዕውቀት ፡ የጥበብ ፡ ጌታ ፡ እንቆቅልሼን ፡ ፍታ

በግመል ፡ ሽቱ ፡ ጭኛለሁ ወርቅና፡ ዕንቁም ፡ ይዣለሁ
ደክሞኛል ፡ ጓዜ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ አድምጠኝ ፡ ያኔ ፡ አርፋለሁ
አገሬን ፡ በዚህ ፡ ወክዬ ፡ ከእግርህ ፡ ስር ፡ ልውደቅ ፡ ጌታዬ

አዝ፦ እኔም ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ነኝ ፡ ብዙ ፡ እንቆቅልሽ ፡ አለኝ
ጌታ ፡ አንተ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ፡ እንቆቅልሽን ፡ መፍታት ፡ ታውቃለህ
የዕውቀት ፡ የጥበብ ፡ ጌታ ፡ እንቆቅልሼን ፡ ፍታ

ሠማይና ፡ ምድርን ፡ ፈጥረሃል ፡ በጥበብህ ፡ ሁሉን ፡ አድርገሃል
ከዓይንህ ፡ የተሰወረ ፡ አሸንፎህስ ፡ የኖረ
ንጉሥ ፡ ሆይ ፡ ኧረ ፡ ምን ፡ ነበር ፡ ፍታልኝ ፡ የእኔንም ፡ ነገር

አዝ፦ እኔም ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ነኝ ፡ ብዙ ፡ እንቆቅልሽ ፡ አለኝ
ጌታ ፡ አንተ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ፡ እንቆቅልሽን ፡ መፍታት ፡ ታውቃለህ
የዕውቀት ፡ የጥበብ ፡ ጌታ ፡ እንቆቅልሼን ፡ ፍታ

ገና ፡ ጥንት ፡ ሳለሁ ፡ በአገሬ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ የሰማሁት ፡ ወሬ
ማመን ፡ ግን ፡ አቅቶኝ ፡ ነበር ፡ ልክ ፡ የለው ፡ የዕውቀትህ ፡ ነገር
ጥበብህ ፡ ከአእምሮ ፡ ያልፋል ፡ ከሰማሁት ፡ ዝናህ ፡ ይበልጣል

አዝ፦ እኔም ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ነኝ ፡ ብዙ ፡ እንቆቅልሽ ፡ አለኝ
ጌታ ፡ አንተ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ፡ እንቆቅልሽን ፡ መፍታት ፡ ታውቃለህ
የዕውቀት ፡ የጥበብ ፡ ጌታ ፡ እንቆቅልሼን ፡ ፍታ

সম্প্রতি দ্বারা শোনা

0 মন্তব্য
    কোন মন্তব্য পাওয়া যায়নি

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads

:: / ::
::
/ ::

কিউ