Yebelay (የበላይ)

ከአንተ ፡ ጋር ፡ የሚቆም ፡ ደፍሮ ፡ የሚወዳደር
(የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ)
አልተገኘም ፡ በምድር ፡ ከጫፍ ፡ ጫፍ ፡ ቢቆጠር
(የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ)
ሥምህ ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ ሥምህ ፡ ይናገራል
(የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ)
የትኛው ፡ ጀግና ፡ ሰው ፡ መቃብር ፡ ፈንቅሏል
(የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ) (፪x)

አዝ:- የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ
በላይ (፫x) ፡ የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ (፪x)

የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ (፬x)

ብዙ ፡ ሃያላንን ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ አይተናል
ማኅደር ፡ ሲገለጥ ፡ ታሪክ ፡ አንብበናል
የትኛው ፡ ጀግና ፡ ነው ፡ ሞትን ፡ ያሸነፈው
ስንቱን ፡ ወንድ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ መቃብር ፡ የዋጠው

አንተ ፡ ግን ፡ ከፍ ፡ ብለሃል
ሞትና ፡ መውጊያውን ፡ ሰብረሃል
ልኩራ ፡ እንጂ ፡ በአንተ ፡ እንዴት ፡ ልፈር
ጌታ ፡ ነህ ፡ ታሪክ ፡ ይናገር (፪x)

አዝ:- የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ
በላይ (፫x) ፡ የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ (፪x)

የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ (፬x)

እስቲ ፡ ይናገሩ ፡ ሰማይና ፡ ምድር
(የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ)
የታሪክ ፡ አዋቂ ፡ ይጠራ/አምጡልኝ ፡ ምስክር
(የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ)
ከአንተ/ከእኔ ፡ጌታ ፡ በላይ : ሞትን ፡ ድል ፡ ያደረገ
(የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ)
እረ ፡ ማነው ፡ እርሱ ፡ በክብር ፡ ያረገ
(የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ) (፪x)

አዝ:- የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ
በላይ (፫x) ፡ የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ (፪x)

የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ (፬x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue