• 195
  • 0
  • 0
  • 4
  • 0

ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ (Liela Liela Liela) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

አዝ፦ ክበር ፡ ብዬ ፡ መቼ ፡ ጠገብኩ
ንገሥ ፡ ብዬ ፡ መቼ ፡ ረካሁ (፪X)
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ (አሃሃ)
ምነው ፡ በኖረና (አሃሃ)
ያንተን ፡ ፍቅር ፡ ምህረት (አሃሃ)
እኔ ፡ ምገልፅበት (፪x)

አይኔ ፡ በርቶ ፡ ሁሉን ፡ አይቶ
ቢናገር ፡ ውስጤ ፡ መቼ ፡ እረክቶ
አልጠገብኩም ፡ አልረካሁም
ክብሬን ፡ ትቼ ፡ ክበር ፡ አልኩህ (፪x)

ይክበር ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ ይክበር ፡ እንጂ
ያገኘሁት ፡ ሰላም ፡ በዚህ ፡ ወዳጅ
ይክበር ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ ይክበር ፡ እንጂ
ያገኘሁት ፡ እረፍት ፡ በዚህ ፡ ወዳጅ

(ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ሲወዳደር ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ
(ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ተሰርቶልኝ ፡ የእኔ ፡ ሥራ
(ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ሌት ፡ እና ፡ ቀን ፡ ብዘምር
(ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ኑሮዬ ፡ ሆኖ ፡ የተአምር (፪x)

ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ (አሃሃ)
ምነው ፡ በኖረና (አሃሃ)
ያንተን ፡ ፍቅር ፡ ምህረት (አሃሃ)
እኔ ፡ ምገልፅበት (፪x)

ላለው ፡ በሰማይ (ሌላ)
ከሰው ፡ ለሚለይ (ሌላ)
ከምለው ፡ በላይ (ሌላ)
ሌላ ፡ አምልኮ (ሌላ)
ምነው ፡ በኖረና (አሃሃሃ)
ለአንተ ፡ ክብር ፡ ዝና (፪x)

ላለው ፡ በሰማይ (ሌላ)
ከሰው ፡ ለሚለይ (ሌላ)
ከምለው ፡ በላይ (ሌላ)
ሌላ ፡ አምልኮ (ሌላ)
ምነው ፡ በኖረና (አሃሃሃ)
ለአንተ ፡ ክብር ፡ ዝና (፪x)

አዝ፦ ክበር ፡ ብዬ ፡ መቼ ፡ ጠገብኩ
ንገሥ ፡ ብዬ ፡ መቼ ፡ ረካሁ (፪X)
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ (አሃሃ)
ምነው ፡ በኖረና (አሃሃ)
ያንተን ፡ ፍቅር ፡ ምህረት (አሃሃ)
እኔ ፡ ምገልፅበት (፪x)

(ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ከዚህም ፡ በላይ ፡ እኔስ ፡ ባወራ
(ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ ለእጅህ ፡ አሻራ
(ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ያንን ፡ ሁሉ ፡ ትተህልኝ
(ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ክብሬን ፡ ብጥል ፡ ሰው ፡ እያየኝ

አምልኮ ፡ ለእርሱ (ለእርሱ)
ክብርም ፡ ለእርሱ (ለእርሱ)
ስግደቴ ፡ ለእርሱ (ለእርሱ)
ለእርሱ ፡ ብቻ (ለእርሱ)
ምነው ፡ በኖረና (አሃሃ)
ለአንተ ፡ ክብር ፡ ዝና (፪x)

አምልኮ ፡ ለእርሱ (ለእርሱ)
ክብርም ፡ ለእርሱ (ለእርሱ)
ስግደቴ ፡ ለእርሱ (ለእርሱ)
ለእርሱ ፡ ብቻ (ለእርሱ)
ምነው ፡ በኖረና (አሃሃ)
ለአንተ ፡ ክብር ፡ ዝና (፪x)

সম্প্রতি দ্বারা শোনা

0 মন্তব্য
    কোন মন্তব্য পাওয়া যায়নি

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads:: / ::
::
/ ::

কিউ