አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ ክንድ ፡ ሆይ ፡ ተነስ (፫x) ፡ በእኛ
ከጥንት ፡ የነበረው ፡ ያ ፡ ታላቅ ፡ ግሩም ፡ ሃይል
ዛሬም ፡ ይንቀሳቀስ ፡ በእኛ (፪x)
ለእስራኤላውያን ፡ የእሳት ፡ ታንኩናቸው
በደመና ፡ ጋርደስ ፡ ከክፉ ፡ አዳንካቸው
እናምናለን ፡ በሃይልህ ፡ በቃልህ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፡ ሃይልህ ፡ ይፍሰስ
አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ ክንድ ፡ ሆይ ፡ ተነስ (፫x) ፡ በእኛ
ከጥንት ፡ የነበረው ፡ ያ ፡ ታላቅ ፡ ግሩም ፡ ሃይል
ዛሬም ፡ ይንቀሳቀስ ፡ በእኛ (፪x)
በምድረበዳ ፡ ቢራቡ ፡ መናን ፡ መግበህ ፡ ጠገቡ
ደግሞም ፡ እንዳይጠማቸው ፡ አስበህ
ከአለት ፡ ውሃን ፡ አፈለቅህ
ልብሳቸው ፡ ነበር ፡ ጌታቸው ፡ ጉልበት ፡ መጠጊያ ፡ ሃይላቸው
አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ ክንድ ፡ ሆይ ፡ ተነስ (፫x) ፡ በእኛ
ከጥንት ፡ የነበረው ፡ ያ ፡ ታላቅ ፡ ግሩም ፡ ሃይል
ዛሬም ፡ ይንቀሳቀስ ፡ በእኛ (፪x)
በሙሴ ፡ ውስጥ ፡ ሆነህ ፡ የሰራህ
የኤልያስ ፡ አምላክ ፡ ወዴት ፡ ነህ
አልረሳንም ፡ ከቶ ፡ ተስፋህን
እንደምሰጠን ፡ ሃይልህን
አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ ክንድ ፡ ሆይ ፡ ተነስ (፫x) ፡ በእኛ
ከጥንት ፡ የነበረው ፡ ያ ፡ ታላቅ ፡ ግሩም ፡ ሃይል
ዛሬም ፡ ይንቀሳቀስ ፡ በእኛ (፪x)