Dagmawi Tilahun--Geta Ale Kegone-Tekekel Ewnetegna (ትክክል ፡ እውነተኛ)

አምኜው ፡ አልከዳኝም
በእኔ ፡ ላይ ፡ አልፈረደም (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ የእኔ ፡ ዳኛ
ትክክል ፡ እውነተኛ (፪x)

ሰው ፡ ፊትን ፡ አይቶ ፡ ሲፈርድ ፡ ጌታ ፡ ግን ፡ የልብን ፡ ነው
ሁሉንም ፡ እንደስራው ፡ አይቶ ፡ ነው ፡ የሚከፍለው
በፍርዱ ፡ አይጸጸት ፡ ለካ ፡ እንዲህ ፡ ነበር ፡ አይል
አስተዋይ ፡ ጥበበኛ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ዳኛ

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ የእኔ ፡ ዳኛ
ትክክል ፡ እውነተኛ (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ፡ ተቀምጦ ፡ በችሎቱ
አይፈራ ፡ አያዳላ ፡ አይዋሽም ፡ እንደሌላ
አፉ ፡ በፍርድ ፡ አይስት ፡ ሚዛኑ ፡ ትክክል ፡ ነው
በእኔ ፡ ላይ ፡ ሳይሆን ፡ ለእኔ ፡ ፈረደልኝ ፡ መድህኔ

ዳኛዬ ፡ እሱ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ዳኛ (፬x)

በግራና ፡ በቀኙ ፡ አማካሪ ፡ አይፈልግም
ቃሉንም ፡ የሚያርመው ፡ ከቶ ፡ አንድም ፡ አይገኝም
እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው ፡ ሥራውን ፡ ይመዝናል
ውሳኔው ፡ መጨረሻው ፡ የእኔን ፡ ልብ ፡ አሳርፏል

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ የእኔ ፡ ዳኛ
ትክክል ፡ እውነተኛ (፪x)

Pinakinggan kamakailan ni

0 mga komento
    Walang nakitang komento

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads:: / ::
::
/ ::

Nakapila