እምቢ ፡ ብዬ (Embi Beyie)

እምቢ ፡ ብዬ ፡ ሰይጣንን ፡ ከድቼው ፡ መጥቻለሁ
በኢየሱስ ፡ ጸንቼ ፡ ለመቆም ፡ መርጫለሁ
አልመኝም ፡ አንዳች ፡ አልፈልግም ፡ በሕይወቴ
ይበቃኛል ፡ የመስቀሉ ፡ ወዳጅ ፡ መድህኔን ፡ እዤ

አዝ፦ ከእርሱ ፡ ውጪ ፡ አልመኝ
አንዳች ፡ ነገር ፡ አያምረኝ
መጥቻለሁ ፡ በፍቅር
ለዘላለም ፡ ለመኖር (፪x)

ብዙ ፡ ወዳጅ ፡ ማከማቸት ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ያጠፋል
ለሁለት ፡ ጌቶች ፡ መገዛትም ፡ ደግሞ ፡ ሁሉን ፡ ያሳጣል
እኔስ ፡ በቃኝ ፡ እንድ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ ፡ ኢየሱሴ
በዚች ፡ ዓለም ፡ የተጐሳቆለው ፡ ስለነፍሴ

አዝ፦ ከእርሱ ፡ ውጪ ፡ አልመኝ
አንዳች ፡ ነገር ፡ አያምረኝ
መጥቻለሁ ፡ በፍቅር
ለዘላለም ፡ ለመኖር (፪x)

ፍቅሩ ፡ የእውነት ፡ የማይለዋወጥ ፡ እጅግ ፡ የጸና
በምህረቱ ፡ ሰውን ፡ የሚያቆመው ፡ ለምሥጋና
ዛሬ ፡ ይኽው ፡ እኔም ፡ ተመርጨ ፡ ዕጣው ፡ ደርሶኝ
ወደቤቱ ፡ መጣሁኝ ፡ ለክብሩ ፡ ቅኔን ፡ ልቀኝ

አዝ፦ ከእርሱ ፡ ውጪ ፡ አልመኝ
አንዳች ፡ ነገር ፡ አያምረኝ
መጥቻለሁ ፡ በፍቅር
ለዘላለም ፡ ለመኖር (፪x)

የዚህን ፡ ዓለም ፡ ብልጽግና ፡ ክብር ፡ ላልመኘው
ጊዜያዊውን ፡ የሚያልፈውን ፡ ነገር ፡ ላልፈልገው
ወስኛለሁ ፡ መርጫለሁ ፡ ጌታ ፡ ይሻለኛል
ለዘላለም ፡ . (1) .

አዝ፦ ከእርሱ ፡ ውጪ ፡ አልመኝ
አንዳች ፡ ነገር ፡ አያምረኝ
መጥቻለሁ ፡ በፍቅር
ለዘላለም ፡ ለመኖር (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue