አዝ:- መልካም ፡ ነህ (፪x) ፡ ሁሉንም ፡ ምሳመር ፡ ትችላለህ (፪x)
ልዩ ፡ ነህ (፪x) ፡ ማሳመር ፡ ማሷብ ፡ ትችላለህ (፪x)
ቅርጽ ፡ ባይኖራት ፡ ማፍራት ፡ ባትጀምር
በመጀመሪያ ፡ ስትሰራት ፡ ምድር
አንድ ፡ ሁለት ፡ ብሎ ፡ በስድስተኛው ፡ ቀን
ጨረስክ ፡ አየኀው ፡ የሰራኀውን
ለብቻህ ፡ ሆነህ ፡ አጋዥ ፡ ሳይኖርህ
ሁሉን ፡ ፈጠርከው ፡ መልካም ፡ አድርገህ (፪x)
አዝ:- መልካም ፡ ነህ (፪x) ፡ ሁሉንም ፡ ምሳመር ፡ ትችላለህ (፪x)
ልዩ ፡ ነህ (፪x) ፡ ማሳመር ፡ ማስዋብ ፡ ትችላለህ (፪x)
ለአብራሃም ፡ ከአገር ፡ ውጣ ፡ ሲለው ፡ ከዘመዶቹ ፡ ሲለያየው
አስቦ ፡ እንጂ ፡ ሊባርከው ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ የሚያስበው
ሁሉ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ አልተባልኩም
መልካም ፡ ይሆናል ፡ አውቃለሁኝ (፪x)
አዝ:- መልካም ፡ ነህ (፪x) ፡ ሁሉንም ፡ ምሳመር ፡ ትችላለህ (፪x)
ልዩ ፡ ነህ (፪x) ፡ ማሳመር ፡ ማስዋብ ፡ ትችላለህ (፪x)
ነገሬን ፡ እርሱ ፡ ሲጀምረው ፡ ቢመስልም ፡ ገና ፡ ቅርጽ ፡ የሌለው
እስኪፈጽመው ፡ እርሱን ፡ ስጠብቅ ፡ ሰጠኝ ፡ ጨርሶ ፡ አሳምሮት
መልካም ፡ ነውና ፡ በባሕሪው
ልዩ ፡ ነው ፡ ጣፋጭ ፡ የሚሰራው
አዝ:- መልካም ፡ ነህ (፪x) ፡ ሁሉንም ፡ ምሳመር ፡ ትችላለህ (፪x)
ልዩ ፡ ነህ (፪x) ፡ ማሳመር ፡ ማስዋብ ፡ ትችላለህ (፪x)
ለአንተ ፡ ያምርልሃል ፡ እስኪ ፡ ስራው
አንተ ፡ አበጃጀው ፡ አሳምረው
ቃሉን ፡ አውጥተህ ፡ ተናገረው
ይሆንልሃል ፡ እንዳሰብከው (፲፬x)