አዝ፦ የተሰዋህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ
የሞትክልኝ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ
ጭንቀት ፡ ጣርህ ፡ ለነፍሴ ፡ ይታይ (፪x)
ሃዘን ፡ ውጦኝ ፡ ሳለሁ ፡ ተጨንቄ
በድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ውስጥ ፡ ወድቄ
ሳላስበው ፡ ድንገት ፡ ኢየሱስ ፡ ጠርቶኝ
የሕይወትን ፡ ውኃ ፡ አፈሰሰልኝ
አዝ፦ የተሰዋህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ
የሞትክልኝ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ
ጭንቀት ፡ ጣርህ ፡ ለነፍሴ ፡ ይታይ (፪x)
የኀጢአት ፡ ሸክም ፡ እጅግ ፡ ጀብዶብኝ
ምንም ፡ አጥቼ ፡ የሚረዳኝ
ኢየሱሴ ፡ ድንገት ፡ ደርሶልኝ
ከድካሜ ፡ ሁሉ ፡ አሳረፈኝ
አዝ፦ የተሰዋህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ
የሞትክልኝ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ
ጭንቀት ፡ ጣርህ ፡ ለነፍሴ ፡ ይታይ (፪x)
በሰይጣን ፡ ሰንሰለት ፡ ታስሬ
ወደገሃነም ፡ እሳት ፡ ሳመራ
ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ ዋስ ፡ ሆኖ
አወጣኝ ፡ ከዚያ ፡ መከራ
አዝ፦ የተሰዋህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ
የሞትክልኝ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ
ጭንቀት ፡ ጣርህ ፡ ለነፍሴ ፡ ይታይ (፪x)
ተስፋ ፡ አልነበረኝም ፡ ከቶ
ከሲኦል ፡ ውስጥም ፡ ለመውጣቴ
በመስቀል ፡ ለእኔ ፡ ሞቶ ፡ አዳነኝ
ያየዋሁ ፡ ቸሩ ፡ አባቴ
አዝ፦ የተሰዋህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ
የሞትክልኝ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ
ጭንቀት ፡ ጣርህ ፡ ለነፍሴ ፡ ይታይ (፪x)