Mesgana Yegebahal(ምሥጋና ፡ ይገባሃል).mp3

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ምህረትህ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ናትና
መንግሥትም ፡ የአንተ ፡ ናት ፡ ጌታ ፡ አምላክ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ይገባሃል ፡ ክብር ፡ ሃሌሉያ

እግዚአብሔር ፡ በመንገዱ ፡ ጻድቅ ፡ ነው
ከቁጣም ፡ የራቀ ፡ ይቅር ፡ ባይ ፡ ነው
ጌታ ፡ እሩህሩህና ፡ መሃሪ ፡ ነው

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ምህረትህ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ናትና
መንግሥትም ፡ የአንተ ፡ ናት ፡ ጌታ ፡ አምላክ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ይገባሃል ፤ ክብር ፡ ሃሌሉያ

ጌታ ፡ በቃሎቹ ፡ ታማኝ ፡ ነው
በስራውም ፡ ሁሉ ፡ ምስጉን ፡ ነው
ለሚጠሩት ፡ ሁሉ ፡ ቅርብ ፡ ነው

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ምህረትህ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ናትና
መንግሥትም ፡ የአንተ ፡ ናት ፡ ጌታ ፡ አምላክ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ይገባሃል ፤ ክብር ፡ ሃሌሉያ

የተፍገመገሙትን ፡ የሚደግፍ
የወደቁትን ፡ የሚያነሳ
ማነው ፡ እንደአንተ ፡ ያለ ፡ አጽናኝ ፡ ጌታ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ምህረትህ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ናትና
መንግሥትም ፡ የአንተ ፡ ናት ፡ ጌታ ፡ አምላክ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ይገባሃል ፤ ክብር ፡ ሃሌሉያ

የሁሉም ፡ ዐይን ፡ አንተን ፡ ተስፋ ፡ ያደርጋል
እጅህን ፡ ትከፍታለህ ፡ ይጠግባሉ
ክቡር ፡ ስምህንም ፡ ያከብራሉ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ምህረትህ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ናትና
መንግሥትም ፡ የአንተ ፡ ናት ፡ ጌታ ፡ አምላክ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ይገባሃል ፡ ክብር ፡ ሃሌሉያ

Lyssnade nyligen av

0 kommentarer
    Inga kommentarer hittades

:: / ::
::
/ ::