Misgana (ምሥጋና)

ሃሌሉያ : ሃሌሉያ : ሃሌሉያ

አሳዳጃችን ፡ ከባሕር ፡ ሰጥሞ
ምድረ ፡ በዳችን ፡ በአንተ ፡ ለምልሞ
ከያለንበት ፡ ተሰብስበናል
እኛም ፡ ሰው ፡ ሆነን ፡ ሰውን ፡ ማርከናል

አዝ፡- ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ከአእምሮያችን ፡ በላይ ፡ ለሆነው ፡ ውለታህ
ቆጥረን ፡ እስከማንዘልቅ ፡ ለበዛው ፡ ስጦታህ
እናከብርሃለን ፡ ክበርልን ፡ ጌታ

በሰው ፡ ልጅ ፡ኀጢአት ፡ ምድርን ፡ብትቀጣ
የመከራ ፡ ጐርፍ ፡ ከላይ ፡ ቢመጣ
በዙሪያችን ፡ አጥር ፡ ሰርተሃል
ለእኛ ፡ ለሕዝብህ ፡ መርከብ ፡ ሆነሃል

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ከአእምሮያችን ፡ በላይ ፡ ለሆነው ፡ ውለታህ
ቆጥረን ፡ እስከማንዘልቅ ፡ ለበዛው ፡ ስጦታህ
እናከብርሃለን ፡ ክበርልን ፡ ጌታ

የፈርኦን ፡ ጦር ፡ ሕዝቡን ፡ አሳዶ
እርሱ ፡ ግን ፡ ቀረ ፡ ከባሕር ፡ ማዶ
እርስታችንን ፡ በድል ፡ ወርሰናል
በአንተ ፡ እረኝነት ፡ እዚህ ፡ ደርሰናል

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ከአእምሮያችን ፡ በላይ ፡ ለሆነው ፡ ውለታህ
ቆጥረን ፡ እስከማንዘልቅ ፡ ለበዛው ፡ ስጦታህ
እናከብርሃለን ፡ ክበርልን ፡ ጌታ

最近收听的

0 注释
    没有找到评论

:: / ::
::
/ ::

队列