• 37
  • 0
  • 0
  • 0
  • 0

Manew (ማነው)

የሰላም ፡ አለቃ ፡ የዘለዓለም ፡ አባት
ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ ፡ የተገባው ፡ ስግደት
ድንቅ ፡ መካር ፡ አምላክ ፡ ሃያልም ፡ ይባላል
ስልጣን ፡ አለቅነት ፡ ለእርሱ ፡ ተሰጥቶታል

አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው
የወደደኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው
የመረጠኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው

ለዘለዓለም ፡ አምካኬ ፡ ነው
ለዘለዓለም ፡ ጌታዬ ፡ ነው
ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ንጉሤ ፡ ነው (፪x)

መንገድና ፡ ሕይወት ፡ እውነትም ፡ ነኝ ፡ ያለው
በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ያለው
ብርታትና ፡ ጥበብ ፡ ኃይልም ፡ የተሞላው
ክብሩ ፡ የገነነ ፡ ምሥጋናው ፡ ብዙ ፡ ነው

አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው
የወደደኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው
የመረጠኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው

ለዘለዓለም ፡ አምካኬ ፡ ነው
ለዘለዓለም ፡ ጌታዬ ፡ ነው
ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ንጉሤ ፡ ነው (፪x)

የክንፉ ፡ መዘርጋት ፡ ምድርን ፡ ይሸፍናል
በሰማይ ፡ ሰማያት ፡ በክብር ፡ ይራመዳል
የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው
በትንሳኤ ፡ በኩል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ነው

አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው
የወደደኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው
የመረጠኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው

ለዘለዓለም ፡ አምካኬ ፡ ነው
ለዘለዓለም ፡ ጌታዬ ፡ ነው
ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ንጉሤ ፡ ነው (፪x)

ሲዘባበቱበት ፡ አፉን ፡ አልከፈተም
በከሳሾቹ ፡ ፊት ፡ ቆሞ ፡ አልተሟገተም
ሞትና ፡ መውጊያውን ፡ . (1) . ፡ ያስቀራል
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ጉልበትም ፡ ይገዛል

አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው
የወደደኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው
የመረጠኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው

ለዘለዓለም ፡ አምካኬ ፡ ነው
ለዘለዓለም ፡ ጌታዬ ፡ ነው
ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ንጉሤ ፡ ነው (፪x)

ከነገድ ፡ ከቋንቋ ፡ ወገኑን ፡ ለይቷል
የሕይወትን ፡ መዝገብ ፡ ማኅተሙን ፡ ፈቷል
ነፍሱን ፡ ቤዛ ፡ ሰጥቶ ፡ ብዙዎችን ፡ ማርኳል
ከሃያላንም ፡ ጋር ፡ ምርኮን ፡ ይካፈላል

አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው
የወደደኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው
የመረጠኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው

ለዘለዓለም ፡ አምካኬ ፡ ነው
ለዘለዓለም ፡ ጌታዬ ፡ ነው
ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ንጉሤ ፡ ነው (፪x)

ኪሩቤል ፡ ሱራፌል ፡ የሚያገለግሉት
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ የሚሉት
ያለ ፡ የነበርነው ፡ ደግሞም ፡ ይመለሳል
ለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ መንግሱ ፡ ይጸናል

አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው
የወደደኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው
የመረጠኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው

ለዘለዓለም ፡ አምካኬ ፡ ነው
ለዘለዓለም ፡ ጌታዬ ፡ ነው
ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ንጉሤ ፡ ነው (፬x)

Lyssnade nyligen av

0 kommentarer
    Inga kommentarer hittades

:: / ::
::
/ ::