Egziabher Birihanena (እግዚአብሔር ፡ ብርሃኔና)

ከባርነት ፡ ቀንበር ፡ ያወጣኸኝ
እስራቴን ፡ ፈተህ ፡ የለቀከኝ
ምሥጋናዬን ፡ እንካ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እንዳንተ ፡ አላየሁም ፡ የሚረታ
የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ነህ ፡ ለተጠማ
እንዲሁም ፡ ብርሃን ፡ በጨለማ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ብርሃኔና ፡ መድሃኔቴ ፡ ነው (፪x)

ቀንበር ፡ ያከበደው ፡ በጫንቃዬ
የነፍሴ ፡ ፈላጊ ፡ ባላንጣዬ
እግዚአብሔር ፡ ከእግሬ ፡ ስር ፡ አስገዛልኝ
እንድቀጠቅጠው ፡ እደረገኝ
እግዚአብሔር ፡ ብርሃኔ ፡ መድሃኔቴ
ሁሌ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ በሕይወቴ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ብርሃኔና ፡ መድሃኔቴ ፡ ነው (፪x)

ማዳኑ ፡ በዛልኝ ፡ ቸርነቱ
ከእኔ ፡ አላራቀም ፡ ምህረቱን
ከመንፈሱ ፡ ዘየትን ፡ እየቀባኝ
በአደባባዩ ፡ አከበረኝ
እዚህ ፡ ደርሻለሁና ፡ በጌታ
አዜምለታለሁ ፡ ጠዋት ፡ ማታ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ብርሃኔና ፡ መድሃኔቴ ፡ ነው (፪x)

የነፍሴ ፡ ፈላጊ ፡ ጠላቶቼ
የበረቱ ፡ አስጨናቂዎቼ
በሞት ፡ ጥላ ፡ እንዳልፍ ፡ ፈረዱብኝ
ግን ፡ ጌታ ፡ ታድጐ ፡ ሕይወትን ፡ ሰጠኝ
ሰልፉ ፡ ቢነሳብኝ ፡ ልቤ ፡ አይፈራም
ጌታ ፡ ብርሃኔ ፡ ነው ፡ ለዘላለም (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ብርሃኔና ፡ መድሃኔቴ ፡ ነው (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue