Minim belelebet (ምንም ፡ በሌለበት)

ምንም ፡ በሌለበት ፡ ጭው ፡ ባለው ፡ በረሃ
አጋር ፡ ከነልጇ ፡ ወደዚያ ፡ ተሰዳ
ተደፍታ ፡ ስታለቅስ ፡ ምርር ፡ ያለ ፡ ለቅሶ
ምንጭ ፡ አፈለቀላት ፡ እግዚአብሔር ፡ ደርሶ [1]

ይደርሳል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይደርሳል
ይደርሳል ፡ የተጠማ ፡ ያያል
ምንጭን ፡ ያፈልቅና ፡ አሜን ፡ ያሳርፋል (፪x)

መጠጥ ፡ እነደጠጣች ፡ ስካር ፡ እንደያዛት
ካህኑ ፡ ኤሊ ፡ እንኳን ፡ ሃናን ፡ ጠረጠራት
እርሷ ፡ ግን ፡ የውስጧን ፡ ችግሯን ፡ ለሚያውቀው
ተናገረችና ፡ ልቧ ፡ በእርሱ ፡ ፀና [2]

ይረዳል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይረዳል
ይረዳል ፡ የውጥን ፡ ይረዳል
የተዘጋን ፡ ከፍቶ ፡ በልጅ ፡ ይባርካል (፪x)

እስራኤላውያኖች ፡ ቀንበር ፡ ከብዶባቸው
የግብፅ ፡ ባርነት ፡ እጅግ ፡ ሰልችቷቸው
ጮሁ ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ እንዲታደጋቸው
እጁን ፡ ዘረጋና ፡ ነፃ ፡ አወጣቸው [3]

ያወጣል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያወጣል
ያወጣል ፡ ነፃነት ፡ ይሰጣል
ከእስራት ፡ ይፈታል ፡ አሜን ፡ ያሳርፋል (፪x)

እመሰክራለሁ ፡ በሕይወቴ ፡ አይቻለሁ
ንብ ፡ ማርን ፡ እንዲከብ ፡ ተከብቤ ፡ ሳለሁ
በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ አምላኬን ፡ ስጣራ
እርሱም ፡ ደረሰልኝ ፡ ጨለማዬም ፡ በራ

ያበራል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያበራል
ያበራል ፡ ጨለማን ፡ ይገፋል
በድንቅ ፡ ይደርስና ፡ አሜን ፡ ያሳርፋል (፪x)

ቀን ፡ በደመና ፡ አምድ ፡ ለሊትም ፡ በእሳት
አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ መምራትን ፡ ሲያውቅበት
ላዘነው ፡ መፅናናት ፡ ለደካማው ፡ ብርታት
ይሄ ፡ ነው ፡ አምላካችን ፡ እስኪ ፡ ዕልል ፡ በሉለት

ይብዛለት ፡ አሁንም ፡ ይብዛለት
ይብዛለት ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት
አሜን ፡ ለአምላካችን ፡ ክብር ፡ ይሁንለት (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue